*=>ረድኤት በረከታቸው ይደርብንና በዚህች ዕለት የካቲት 1 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉ አባታችን አቡነ እንድርያስ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፦*
አንድ ብዙ ኃጢአት የሚሰራ ሠው ነበረ እንዲህ ሲኖር የቁስል በሽታ ይዞት የፊቱ መልክ እስኪለወጥ እግሩም እንደ ዝሆን እግር እስኪሆን ድረስ አካሉ ሁሉ አበጠ። ቤተ ሰቡና ዘመዶቹም ሙተህ በቀበርንህ በተሻለን ነበር ብለው አለቀሱለት። ሰውየውም አልቅሶ ለዘመዶቹ ወደ መንደሮች ሄዳችሁ ባለ መድኃኒትን ፈልጉልኝ ካገኛችሁም አምጡልኝ አላቸው፡፡ አንዳላቸውም ሔደው አመጡለት፡፡ ባለ መድኃኒቱም አይቶ «ላድነው አይቻለኝም አለ። ቤተሰቡም ሰምተው ከቀድሞ ይልቅ አምርረው አለቀሱ። እያለቀሱ ሳሉም አንድ ሰው መጥቶ ምን ያስለቅሳችኋል አላቸው፡፡ እነሱም ወንድማችን በቊስል ደዌ ታሞአል፤ ባለ መድኃኒትም ላድነው አልችልም ብሎአል አሉት። ሰውየውም አታልቅሱ ወንድማችሁን የሚፈውሰውን እኔ እነግራችኋለሁ፤ እኔም በቁስል ደዌ ተይዤ ሊፈውሰኝ የሚቻለው ያለ እንደሆነ ለማግኘት ከአገር አገር ለዓመታት ሔድኩኝ፡፡ ዳሩ ግን አላገኘሁም። አንድ ቀን ከአገሩ ሰዎች እኔን አይተው ለእንደዚህ በሽታ ኣቡነ እንድርያስ ጸበል ጸበል በቀር ሊፈውሰው የሚችል የለም ብለው ሲናገሩ ሰማሁ፡፡ እኔም ያገሩ መንገድ ጠይቄያቸው ሔድኩ። በዚያ ብዙ በሽተኞች አግኝቼ ከነሱ ጋር ታጠብኩኝ ከመቃብር ቦታውም ጠበል ተቀባሁ።አሁን እንደምታዩኝ ተፈወስኩ ብሎ ቆስሎ እንደ ነበረ ኋላም እንደ ዳነ የእጁና የእግሩ ጣቶች አሳያቸው:: _ ዘመዶቹና በሽተኛውም አይተው ደስ ብሎአቸው ሰውየውን «የዚች ገዳም መንገድ እንድትመራን እንማፀንሃለን» አሉት። እሱም እሺ እዚያ አደርሳቸዋለሁ አላቸው በንጋታውም ተነሥተው በበቅሎ አስጭነው የዳነው ሰውዬ እየመራቸው እዚያ ደረሱ፡፡ በሽተኛውም እዛው ከደረሰ በኋላ ቤተክርስቲያን ገባ በአባታችን መቃብር ቦታም ሰግዶ አባቴ ሆይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት አንድትለምንልኝ እማጸንሀለሁ ወደ ገዳምህ መጥቶ በዋሻህ ካለ ውኃ የታጠበ ከመቃብር ቦታህም የተቀባ ይድናል ብሎ የምሕረት ቃል እንደ ሰጠህ ሰምቻለሁና፤ እኔም ከኔ በፊት በነበሩ አባቶቼና ዘመዶቼ ያልነበረ ለኔ ግን በኃጢአቴ አገኘኝ ይህን ጽኑ ደዌ ያድነኝ ዘንድ ከእግዚአብሔር ምሕረት ትለምንልኝ ዘንድ እማፀንሃለሁ አሁንም አባቴ ሁሉ ያመለከትከው እንደሚሰጥህ መና ማውረድም ማይደንቅህ/እንደማይሳንህ/ አውቃለሁና ከበሽታና ኵነጢአት ማሰሪያ እንድትፈታኝ እለምንሃለሁ ብሎ : ከመቃብር ቦታው ጸበል ተቀባ፡፡በሦስተኛው ቀንም የመዳን ምልክት አሳይቶ ከደዌው ተፈወሰ፡፡ ዘመዶቹም አይተው ሐሴት አደረጉ፤ በቅዱሳኑ
የሚመሰገን የምስጋና ጌታ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡
+++
ዳግመኛም አቡነ እንድርያስ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው :-አንድ በብርቱ ደዌ የሚሰቃይ በክፉ አጋንንት እየተገዛ የሚኖር ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ፡፡ ያብዳል ልብሶቹን ቀዶም ራቁቱን ይሆናል፡፡ ቤተሰቡና ዘመዶቹም ይዘው ቀን ተሌሊት እጆቹንና እግሮቹን በማሰር ደከሙ፡፡ አንድ ቀን በብረት ሠንሰለቶች አስረው ወደ አባታችን እንድርያስ ገዳም አመጡትቤተ ክርስቲያን አግብተውም የአባታችንን ገድል አንብበው ከሕይወት ውኃ ቢያጥቡት ከመቃብሩም ጠበል ቢቀቡት ህዝቡ ሁሉ እያዩ ከእንግዲህ ወዲህ ከእሱ እንደምወጣ ዳግመኛም እንዳላሳብደው - እምላለሁ ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ፈጽሞ ጮኸ። ያን ጊዜ ከእርሱ ወጣ እንደ ፊተኛው ሕይወቱም ጤነኛ ሆነ፡፡ ከዳነ በኋላ አባቱ ያለ ፈቃዱ ሴት ልጅን አጨለት፡፡ ወጣቱ አባቱ እንዳጨለት አውቆ በሌሊት ካባቱ ቤት ወጥቶ በአንድ ገዳም ገብቶም ይህን አላፊ ዓለም ንቆ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በጾም በጸሎት ተወስኖ በገዳማዊ ሥራዎች መላላክ ተጠምዶ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሆነ የዚህ ተአምር አድራጊ አባታችን ልመናው ይደረግልን በረከቱም ይደርብን ከነጣቂ ወራሪም ይስውረን ለሁላችን ለማኅበር ልጆች ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
ዳግመኛም አባታችን አቡነ እንድርያስ ያደረገው ተአምር ይህ ነው።አባታችን እንድርያስ ወደ አንድ ገዳማዊ አባ ገብረ ክርስቶስ የተባለ መነኩሴ በሚጓዝበት ጊዜ ተንቤን የተባለ ቦታ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ገባና ቆሞ መጸለይ ጀመረ።እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ ከእግሩ ስር በጣም የጠራ ውሃ ፈለቀና ለብዙ ድውያንና ሕሙማን መድኃኒት ሆነ።ከዚህ በኋላ ይህች ከእግሩ በታች የፈለቀች ውሃ የድኅነት ቦታ ተብላ ተጠራች እስከ አሁንም ብዙ የሚደነቅ ተአምር እየተፈጸመባት ትገኛለች።
ረድኤት በረከታቸው ትደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
(ምንጭ ገድለ አቡነ እንድርያስ ደብረ መድኃኒት አቡነ እንድርያስ ቤተ ክርስቲያን ሴሮ መቃይሕ ያሳተመው)
✞ ✞ ✞