አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 9-ሰማዕቱ ቅዱስ ጳውሎስ ሶሪያዊ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ከሃድያን ይዘው ምላሱን በመቁረጥ፣ በእሳት በማቃጠል፣ የብረት ችንካሮችን በእሳት አግለው በአፉና በጆሮዎቹ የቸነከሩበትና በመጨረሻውም አንገቱን የሰየፉት ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡
+ በሶርያ አገር ላሉ መነኮሳት ሁሉ አባት የሆነ ታላቁ አባ በርሱማ ዐረፈ፡፡ እርሱም እንደ ኢያሱ ፀሐይን ገዝቶ ያቆመ፣ ዝናብንም በጸሎቱ ያዘነበ ነው፡፡ ንስጥሮስን ካወገዙትና ሃይማኖታችንን ከጠበቁልን አባቶች አንዱ ሲሆን ከሃድያን በክፋታቸው አሠቃይተውታል፡፡ በድንጋይም ወግረው ሊገድሉት ቢሉ የወረወሩት ድንጋይ ወደ ራሳቸው ወደ ወርዋሪዎቹ የሚመለስ ሆነ፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የመነኮሱበት በዓል ነው፣፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ጳውሎስ ዘሶርያ፡- ወላጆቹ በሶርያና በእስክንድርያ የሚኖሩ ሀብታም ነጋዴዎች ነበሩ፡፡ እነርሱም በጣም ብዙ ገንዘብ ትተውለት ሞቱ፡፡ በወቅቱ ከሃዲያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቶስ ያመኑትን ሁሉ እያሠቃዩ እንሚገድሏቸው በሰማ ጊዜ ተነሥቶ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት መንገዱን ይመራው ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለየ፡፡
ጌታችንም መልአኩ ቅዱስ ሱርያልን ላከለትና ስለ ስሙ የሚደርስበትን ጽኑ መከራና ሥቃይ በመጨረሻም የክብር አክሊልን እንደሚቀዳጅ ነገረው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወዲያው ተነሥቶ ወደ እንዴና ከተማ ሄዶ በከሃዲው መኰንን ፊት ስለ ጌታችን ክብር መሰከረ፡፡ መኰንኑም ይዞ ራቁቱን አሠቃቂ ግፍርፋትን ካስገረፈው በኋላ በእሳት እንዲያቃጥሉት አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም ቅዱሱን በእሳት ለበለቡት፡፡ በሌላም ጊዜ መኰንኑ ቅዱስ ጳውሎስን ከእሥር ቤት አውጥቶ ለጣዖቱ እንዲሠዋ በማባበል ብዙ ገንዘብ አመጣለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ወላጆቼ ሲሞቱ ያወረሱኝን ብዙ የወርቅ ወቄት ሽጨ ለድኆች መጽውቼ በጌታዬ ስም የታመንኩ ሰው እንዴት ወደተናቀ ያንተ ገንዘብ እመለሳለሁ›› በማለት የረከሱ ጣዖታቱንም ጨምሮ ረገመበት፡፡ መኰንኑም በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ የብረት ችንካሮች በእሳት አግሎ በአፉና በጆሮዎቹ ቸነከረበት፡፡ አሁንም መልአኩ ቅዱስ ሱርያል መጥቶ ከሕማሙ ሁሉ ፈወሰው፡፡ ዳግመኛም መኮንኑ መርዛማ እባቦችን በላዩ ሰደዱበት ነገር ግን እባቦቹ አልነኩትም፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ እየመሰከረና በሚያደርጋቸው ተአምራትም ብዙዎችን ስላሳመነ እንዳይናገር ብለው ምላሱን ቆረጡት፤ ነገር ግን ጌታችን አዳነው፡፡ በመጨረሻም መኰንኑ ከእንዴና ወደ እስክንድርያ ወስዶት በዚያ ብዙ ካሠቃየው በኋላ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም አስቀድሞ መልአኩ ቅዱስ ሱርያል እንደነገረው ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ የክብር አክልን ተቀዳጀ፡፡ ዕረፍቱም የካቲት 9 ሆነ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
አባ በርሱማ፡- የዚኽም ወላጆቹ ሳሚሳጥ ከሚባል አገር የተገኙ ናቸው፡፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ የሚኖር አንድ ደገኛ ጻድቅ አባ በርሱማ ከመወለዱ አስቀድሞ ስለ እርሱ ለአባቱ ትንቢት ነገረው፡፡ ‹‹የትሩፋቱ ዜና በሶርያ አገር ሁሉ የሚሰማ ጣዕም ያለው ፍሬ ከአንተ ይወጣል›› በማለት የሚሆነውን ሁሉ አስረዳው፡፡
አባ በርሱማ በተወለደ ጊዜ እግዚአብሔርን ወደማወቅ ሲመጣ ከወላጆቹ ሸሽቶ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ደርሶ በዚያ ስሙ አብርሃም ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጠ፡፡ እርሱም ወላጆቹን ስለፈራ ከዚያ ገዳም ሰደደውና አባ በርሱማ ሄዶ በአንድ ዓለት ውስጥ ገብቶ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ ከትሩፋት ተጋድሎውም ብዛት የተነሣ ዜናው በሶርያ አገር ሁሉ ተሰማ፡፡ ብዙ ደቀመዛሙርትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፡፡ ነገር ግን በዚያ ቦታ ላይ ያለው ውኃ እጅግ መራራ ነበር፡፡ አባ በርሱማም ደቀ መዛሙርቱ በተሰበሰቡ ጊዜ በውኃው ላይ ጸልዮ እጅግ መራራ የነበረውን ውኃ ለውጦ ግሩም ጣዕም ያለው አደረገው፡፡ እግዚአብሔር ሌሎች ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በአባ በርሱማ እጅ አደረገ፡፡ በአንዲትም ዕለት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከበዓቱ ርቆ ሳለ የፀሐይ መግቢያ ሰዓት ደረሰ፡፡ አባ በርሱማም ወደ ጌታችን በጸለየ ጊዜ ወደ በዓቱ እስኪደርስ ድረስ ፀሐይ ቆመችለት፡፡
በሌላም ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- ረዓም የምትባል አገር ነበረች፡፡ ሰዎቿም ከሃዲዎች ናቸው፡፡ በላያቸውም ዝናብ የተከለከለ ሆነ፡፡ በተጨነቁም ጊዜ ወደ አባ በርሱማ መጥተው ለመኑት፡፡ እርሱም ስለ ክህደታቸው ገሠጻቸውና ‹‹በእግዚአብሔር ብታምኑ ዝናብን ያዘንብላችኋል›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አሁን በአንተ ጸሎት ዝናብ ካዘነበልን እናምንበታለን›› አሉት፡፡ አባ በርሱማም ወደ ጌታችን በጸለየ ጊዜ ለእነዚያ ሰዎች ወዲያው ዘነበላቸው፡፡ እነርሱም በጌታችን አመኑ፡፡ እንደዚሁም ሰዎቿ ከሃድያን የሆኑ ሌላ አገረ ነበረች፡፡ አባ በርሱማ ወደ እነዚህ ሰዎች ሄዶ በቃሉ ትምህርትና በተአምራቱ እግዚአብሔርን ወደማወቅ መለሳቸው፡፡ የጣዖቶቻቸውንም ቤቶች አፈረሰ፡፡
አባ በርሱማ የጸሎት ቦታ አዘጋጅቶ በዚያ ሳይቀመጥ 54 ዓመት ቆሞ በተጋድሎ ኖረ፡፡ በደከመውም ጊዜ ግድግዳ ተደግፎ ያንቀላፋል እንጂ አልተቀመጠም፡፡ በየሰባት ቀኑም ይጾማል፡፡ የከበረ አባ ስምዖን ዘዓምድ የዚህን የአባ በርሱማን ዜና ሰምቶ ሊያየውና ሊባረክ ስለወደደ መልእክተኛ ላከበት፡፡ ይኸውም እጅግ የከበሩ አባ ስምዖን ዘዓምድ ሰውነታቸውን እጅግ ከመጉዳታቸው የተነሣ ሊጎበኟቸው የሚመጡት ቅዱሳን የሞቱ ይመስላቸው ነበር፡፡ የክርስቶስን መታሰርና መቸንከር አስበው ሰውነታቸውን በቀጭን ገመድ አጠላልፈው በጣም በኃይል አጥብቀው ስላሰሩት ገመዱ የሰውነታቸውን ሥጋ እየቆራረጠ ይጥለው ነበር ከቁስሉም የሚወጣው ደምና መግልም እየሸተተ ቢያስቸግራቸው መነኮሳቱ ሳይቀሩ ይገፏቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ስምዖን ቁመቱ ስልሳ ክንድ የሆነ የድንጋይ ምሰሶ ላይ ወጥተው በዚያ ሆነው ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረጉ፣ ሕሙማንን እየፈወሱ፣ ወንጌልን ሳይቀመጡ ቆመው እያስተማሩ 12 ዓመት የኖሩ ናቸው፡፡ አባ ስምዖን አባ በርሱማን ለማየትና በረከትን ለመቀበል ሽተው መልዕክተኛ ሲልኩባቸው አባ በርሱማ ሄደና አገኛቸው፡፡ እርስ በእርሳቸውም በረከትን ከተቀባበሉ በኋላ አባ በርሱማ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡
ከዚህም በኋላ አባ በርሱማ በሶርያ አገር እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰበከ፡፡ በፊታቸውም ብዙ ተአምራትን እያደረገና እያስተማረ ብዙዎችን አሳመናቸው፡፡ ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ (ታናሹ) ዘንድ በመሄድም በቀናች ሃይማኖት ጸንቶ እንዲኖርና ፈሪሃ እግዚአብሔርን አስተማረው፡፡ ንጉሡም ብዙ ወርቅ ቢሰጠው አባ በርሱማ ግን አልወስድም አለ፡፡ ከዚህም በኋላ በአንጾኪያም አገር ላይ በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ሥልጣን እንዲኖረው ንጉሡ ጻፈለት፡፡ ለዚህም ምልክት ቀለበቱን ሰጠው፡፡ በከሃዲው ንስጥሮስ ምክንያት 200 የከበሩ ቅዱሳን ሊቃውንት በኤፌሶን በተሰበሰቡ ጊዜ ይህም ቅዱስ አባ በርሱማ ከእነርሱ አንዱ ነው፡፡ ከሌሎቹም ቅዱሳን ሊቃውንት ጋር ሆኖ ንስጥሮስን አወገዘው፡፡ ዳግመኛም ንጉሡ በአንጾኪያ አገር ያሉ መኳንንት፣ መሣፍንትና ሹማምንት ሁሉ ለአባ በርሱማ እንዲታዘዙለት ደብዳቤ ጻፈ፡፡ አባ በርሱማም በበጎ ሥራ ሁሉ እንደበረቱ በሃይማኖትም እንዲጸኑ የሚያዝ ደብዳቤ በመጻፍ በንጉሡ ቀለበት እያተመ ለሀገሮች ሁሉ ይልክ ጀመር፡፡ በዚህም ጊዜ ክፉዎች ሰዎች አባ በርሱማን ጠሉት፡፡ ወደ ንጉሡም ዘንድ ገብተው ‹‹አባ በርሱማ እንደ ዓለም ሰው ሆኖ ይበላል ይጠጣል፣ መልካም ልብስንም ይለብሳል›› ብለው