ነገር ሰሩበት፡፡ ንጉሡም ይህንን ያረጋግጥ ዘንድ ከጭፍሮቹ አንዱን በድብቅ ይከታተል ዘንድ ወደ አባ በርሱማ ላከው፡፡ ያም የተላከው አባ በርሱማን ከቀድሞው የተለየ ሆኖ ስላላገኘው ሄዶ ለንጉሡ ነገረው፡፡ ንጉሡም አባ በርሱማን ወደ እርሱ አስመጥቶ ባየው ጊዜ በሁሉም ነገር እንደቀድሞው ሆኖ ቢያገኘው ዳግመኛም ታላቅ ክብርን አከበረውና ወደቦታው መለሰው፡፡
መናፍቁ ንጉሥ መርቅያን የኬልቄዶንን ጉባኤ በሰበሰበ ጊዜ የንጉሡ አማካሪዎች አባ በርሱማን እንዳያስመጣ ንጉሡን መከሩት፡፡ ምክንያቱም ጉባኤያቸው የሐሰትና የክህደት ስለሆነ አባ በርሱማም ንጉሡን ሳይፈራና ሳያፍር ለሰው ፊትም ሳያደላ ተከራክሮ ረቶ እንደሚያሳፍራቸው ስለሚያውቁ ነው፡፡ እነርሱም የክብርን ባለቤት አንዱን ክርስቶስ ኢየሱስን ወደ ሁለት የከፋፈሉበት ይህ ጉባኤያቸው በተፈጸመ ጊዜ የከበረ አባ በርሱማ ተጣላቸው፡፡ በመንቀፍና ቃላቸውንም በመሻር አወገዛቸው፡፡ እነርሱም ወንጅለው በጽሑፍ አድርገው ወደ ንጉሡ ከሰሱት፡፡ ንጉሡም አባ በርሱማን ወደ እርሱ አስመጣው ነገር ግን በላዩ ያደረ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ስላለ ሊቃወመው አልቻለም፡፡ በዚህም ጊዜ አባ በርሱማ በሊቁ በቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ ስላደረገችው የክፋት ሥራና ግፍ ንግሥቲቱን ረገማት፡፡ እርሷም ጥቂት ጊዜ ቆይታ በክፉ አሟሟት ሞተች፡፡
ከዚህም በኋላ መናፍ*ቃኑ አባ በርሱማን የሚቃወመት ሆኑ፡፡ ምእመናን ሁሉ እንዳይታዘዙለት በአገሮች ሁሉ ጽፈው ላኩ፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ አልተቀበላቸውም ነበር፡፡ ዳግመኛም አባ በርሱማን በጎዳና ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ 200 መናፍ*ቃን ሰዎች ከመናፍ*ቃን ኤጲስቆጶሳት ጋር ተስማሙ፡፡ በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ ጠየቁትና አብረው ሲጓዙ በመንገድ ላይ ሳሉ ሁሉም ትላልቅ ድንጋዮችን አንስተው በአባ በርሱማ ላይ ጣሉ ነገር ግን ድንጋዮቹ በተአምራት ወደራሳቸው ወደ ወርዋሪዎቹ እየተመለሱ ብዙዎቹን አቆሰሉ፡፡ በዚህም ጊዜ በፍርሃት ከእርሱ ሸሹ፡፡
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር አባ በርሱማን ከዚህ ዓለም ሊወስደው በወደደ ጊዜ መልአኩን ወደ እርሱ ልኮ ከ4 ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም እንደሚያርፍ ነገረው፡፡ በዚህም ጊዜ አባ በርሱማ በዙሪያው ወዳሉ አገሮች ሁሉ ምእመናንን ያጽናና መልእክትም ያደርስ ዘንድ ረድኡን ላከው፡፡ ረድኡም ሲዞር የከበረች የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ወደምትኖርበት ቦታ ደረሰና እጅ ነሣት፡፡ እርሱም በዚያ ስለ ከሃዲው ንጉሥ መርቅያን እያለቀሰ ሲለምን ከመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ‹‹አባ በርሱማ ወደ እግዚአብሔር ስለከሰሰው ያ ከሃዲ መርቅያን ሙቷልና አትፍራ›› የሚል ቃል ወጣ፡፡ ረድኡም ይህን ሲሰማ እጅግ ደስ ብሎት መልእክቱን አድርሶ ምእመናንን አጽናንቶ ወደ አባቱ ዘንድ ተመለሰ፡፡ አባ በርሱማም ረድኡን ባረከውና በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ከበዓቱም ደጃፍ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታየ፡፡ ምእመናንም ሁሉ ይህንን ከሩቅ አይተው ወደ እርሱ መጡ፡፡ እርሱንም ዐርፎ አገኙትና ከሥጋው ተባረኩ፡፡ ከእነርሱም ስለመለየቱ እጅግ አዘኑ፡፡
የአባ በርሱማ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
(የቅዱሳን ገድላቸውን ተአምራታቸውን በየቀኑ በቴሌግራም ቻናል በኩልም ይከታተሉ።