እብዱ ዮሐና
....................ምዕራፍ ስምንት(9)
በጭራሽ አልደፈረሰም:: ለኢየሱስ ያለው ፍቅርም በፍጹም አልተለወጠም፡፡ ስቃይ ሀቀኛ ሰውን አይጐዳም፣ የጭቆና ቀንበርም ከእውነት ጐን የቆመን ሰው ጨፍጭፎ አያጠፋውም፡፡ በግፍ የሚያሰቃዩት እጆችም የልቡን ሰላም ሊወስዱበት አይችሉም:: ሶቅራጦስ ከዕፅዋት የተቀመመውን _ መርዝ በፈገግታና በኩራት አልነበረም እንዴ የተጐነጨው? ጳውሎስ ለእውነት ብሎ በልበ ሙሉነት በድንጋይ አልተወገረምን?
አዎን፣ አንታዘዝም ስንል የሚጐዳንና ስንክድ የሚገድለን ውስጣችን ነው፡፡ ህሊናችንን ስንቃወመው ነው የሚጐዳን፤ ስንከዳውም _ ነው የሚፈርድብን፡፡
*
የዮሐና ወላጆች ብቸኛው ልጃቸው ከብቶቹ ተወስደውበት እንደታሰረ ሰሙ:: አሮጊቷ እናቱ በከዘራቸው ድጋፍ ወደ ገዳሙ መጡና ቄስ-ገበዙ እግር ላይ ተደፉ:: አይኖቻቸው በእንባ እየታጠበና የቄስ-ገበዙን እጆች እየሳሙም፣ ለልጃቸው እንዲያዝኑለትና ባለማወቅ _ ለፈፀመው ተግባር ምህረት እንዲያደርጉለት ተማፀኗቸው፡፡
ቄስ-ገበዘ ከዓለማዊ ጉዳዮች በላይ እንደሆኑ ሁሉ ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ሰቀሉና፣ «እኛ የልጅሽን ንግግር ይቅር ብለን ጅልነቱን በቸልታ ልናልፈው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ገዳሙ መክፈል የሚገባውን ሂሣብ የመጠየቅ ቅዱስ መብት አለው:: እኛ ጨዋ በመሆናችን የሰዎችን ህግ የመተላለፍ ተግባር ይቅር ብንልም፣ ሃያሉ ነቢይ ኤልያስ ግን ወደ ወይን ተክሎቹ ውስጥ አልፈው የሚገቡትንና በመሬቱ ላይ እንስሶቻቸውን ለግጦሽ የሚያሰማሩትን በፍጹም ይቅር አይላቸውም፣ አይምራቸውምም!» አሉዋቸወ፡
አሮጊቷ እንባቸው በተጨማደደው ጉንጫቸው ላይ ቁልቁል እየወረደ፣ ገና እንባ በተሞሉም ዓይኖቻቸው ቄስ - ገበዙን ቀና ብለው ከተመለከቷቸው በኋላ ከአንገታቸው ላይ ትንሽ የብር ሃብላቸውን አውልቀው በቄስ - ገበዙ እጅ ላይ አስቀመጡ፡፡ «አባቴ ከዚህ ሀብል በስተቀር ምንም ነገር የለኝም፡፡ ያለኝ ውድ ንብረት ይሄ ብቻ ነው:: የሰርጌ ዕለት እናቴ የሰጠችኝ ስጦታ ነው፡፡ ምናልባት ገዳሙ ብቸኛው ልጄ ለፈፀመው ጥፋት ይሄንን እንደ ንስሀ ይቀበለኝ ይሆን?»
ቄስ-ገበዘ- ሀብሉን ኪሳቸው ውስጥ የከተቱት ጊዜ እናቲቱ ምስጋናቸውን እያዥጐደጐዱ የቄሱን እጅ መላልሰው መሳም ጀመሩ፡፡
ቄስ-ገበዙ ትክ ብለው ተመለከቷቸውና፣ «ለዚህ ሀጢያተኛ ትውልድ ወዮለት! የመፅሀፉን ትዕዛዛት በመቃወማቸው መራራውን ፍሬ እንዲጐነጩ ሆነዋል::
..........ይቀጥላል..........
👍👍👍👍👍👍👍👍
https://t.me/Asresee