#ከርእስ_ውጪ_የግል_እይታ
ከሁለት ወራት በፊት ተካሂዶ ከነበረው የባሎንዶር ሽልማት በላይ የዛሬው የግሎብ ሶከር አዋርድ አሳፋሪ ነው። ዛሬ በግልጽ በባሎንዶር ተበዳይ ነን ባዮቹን ሬያል ማድሪድን እና ቪኒሲየስን የመካስ ዓላማ ነበር የነበራቸው። ጭራሽ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በንግግሩ ሮድሪ ሽልማቱ እንደማይገባው እና ግሎብ ሶከር በአንጻሩ እውነተኛ ሽልማት መሆኑን ተናግሯል።
የሬያል ተጫዋቾች ያሸነፏቸው አንዳንድ ሽልማቶች ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው። ለምሳሌ ቪኒሲየስ ጁኒየር የዓመቱ ምርጥ አጥቂ እና የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በሚል ተሸልሟል። የዓመቱ ምርጥ አጥቂ ሽልማትን ብዙ ጎል ያስቆጠረው እንግሊዛዊው ሀሪ ኬን ማሸነፍ ይገባው ነበር ምክንያቱም ሁላችንም እንደምናውቀው ቪኒሲየስ የ40 ጎሎች አጥቂ አይደለም።
በሌላ በኩል ጁድ ቤሊንግሃም ሮድሪ ባለበት ውድድር የዓመቱ ምርጥ አማካይ መባሉ ሳያንስ የማራዶና አዋርድ አሸናፊ ሆኗል። ቲቦ ኮርቷ ምንነቱ የማይታወቅ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። ግሎብ ሶከር ያለ ወትሮ የምንጊዜም ምርጥ ፕሬዝደንት ሽልማትን ለፊዮረንቲኖ ፔሬዝ ሰጥቷል።
በአጠቃላይ ደስ የማይል ዝግጅት እንደነበር ለመረዳት የላሚንን ፊት ማየት በቂ ነው። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የግል እይታ ብቻ ነው።
@BARCAFANSETHIOPIA