ብራዚል ተማሪዎች ስልክ እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ አወጣች
በመጀመሪያ እና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ተማሪዎች ስልክ እንዳይጠቀሙ በሚገድበው ሕግ ላይ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ፊርማቸውን በረቂቅ ህጉ ላይ አኑረዋል፡፡ የብራዚል ትምህርት ሚኒስትር ካሚሎ ሳንታና ልጆች በሕጻንነታቸው ስልክ በመያዝ ከዕድሜያቸው ጋር ላልተጣጣመ መረጃ ይዳረጋሉ ብለዋል፡፡
ማህበራዊ ሚዲያው ከሚያሳድርባቸው ጫና አንጻር አስተዳደጋቸውን ለመከታተል ለወላጆች አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረው አዲሱ ህግ ይህን እንደሚቀርፍ አስታውቀዋል፡፡ በመጀመሪያ እና በከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ተማሪዎች ስልክ እንዳይጠቀሙ ገደብ የሚጥለው አዲሱ ረቂቅ ህገ ለአስገዳጅ ሁኔታዎች ብቻ ስልክ መጠቀምን የሚፈቅድ ነው ተብሏል፡፡ ለድንገተኛ አደጋዎች፣ በመምህራን መሪነት ለትምህርት ጉዳዮች እና ስልክ መያዝ አስገዳጅ ለሚሆናቸው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ህጉ ይፈቅዳል፡፡
ህጉ በበርካታ ወላጆችና ተማሪዎች በኩል በጎ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በረቂቁ ላይ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ላይ የተሳተፉ ከ66 በመቶ በላይ የሚሆኑት ስልክ ከተማሪዎችና ከታዳጊዎች ለማራቅ በመንግስት በኩል የተደረሰው ውሳኔ ተገቢ ነው ማለታቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
(መረጃው የ EDL ነው)
ይህ ሁኔታ የሚያሳዬው ስልክ በተለያዩ ያደጉ ሀገራት ጭምር በልጆች አስተዳደግ ላይ በተለይም በተማሪዎች ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ነው።
ስለሆነም ተማሪዎቻችን ከስልክ ጋር የሚኖራችሁ ግንኙነት የተገደበ፣ ለትምህርታዊ ፕሮግራሞችና ዘመናዊ የትምህርት ቴክኖሎጂን ለመጠቀም መሆን ይኖርበታል።