⁉️ሚሊየነር(ቢ) መሆን ትፈልጋለህ
‼️ሽያጭን ተማር ጽናት ይኑርህ
▶️ፊልሙን እየው
⭐ያለፈበት ህይወት 55 ሚሊየን ዶላር ተመድቦለት የሚሰራ ፊልም ይሆናል ብሎ አንድም ቀን አስቦ አያውቅም
.....
✅ ክርስቶፎር ጋርድነር ፡ በየክሊኒኩ በእግሩ እየዞረ በኮሚሽን የሚሸጣቸውን የህክምና መሳሪያዎችን ይዞ እየሄደ እያለ በመንገዱ ላይ. . ዋጋው ውድ የሆነ ፡ ቀይ ፌራሪ መኪና ቆሞ ያያል ።
እና ወደ ባለመኪናው ሰው ጠጋ ብሎ ሰላምታ ካቀረበለት በኋላ ፡ ይህንን መሳይ ውድ መኪና መንዳት የቻልከው ስራህ ምን ቢሆን ነው ሲል ጠየቀው ።
.....
✅ ይህ ሰው Bob Bridges ይባላል ፡ የአክስዮን ሽያጭ ባለሙያ ነው ፡ እና በቅንነት ቀርቦ ለጠየቀው ክሪስ ጋርድነር ይህንኑ ነገረው ።
ፍላጎቱ ካለው ፡ እሱም ይህንን መስራት እንደሚችልም ገለፀለት ጋርድነር አላንገራገረም ። ወዲያው የአክስዮን ሽያጭ ባለሙያ ለመሆን ተመዘገበ ። ችግሩ በዚህ የተለማማጅነት ወቅት ምንም የሚከፈለው ገንዘብ አልነበረም ።
...
✅ በዚህም ምክንያት ነገን እያሰበ በነጻ አክስዮን ገዥ ሲፈልግ የሚውለው ጋርድነር የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶት ከልጁ ጋር ጎዳና ወጣ ።
የሁለት አመት ከወራት እድሜ ያለው ልጁን ይዞ ጎዳና የወጣው ጋርድነር የጎዳናው ብርድ ሲበረታ ወደ ባቡር ጣቢያ ይሄድና ፡ መፀዳጃ ቤት ገብተው ይተኛሉ ።
በመናፈሻ ስፍራዎች ውስጥ. .. በቤተክርስቲያን አንዳንዴ ደግሞ ፡ ከሚሰራበት ካምፓኒ ቢሮ ሰራተኞች ሲወጡ ይጠብቅና ጠረጴዛ ስር. ተኝተው ለሊቱን ያሳልፋሉ ።
....
✅ ክሪስ ጋርድነር ትንሹ ልጁን በኮቱ ሽፍን አድርጎ በጎዳና ላይ በሚተኛበት በዛን ወቅት. .. እያለ አንድ ቀን ይህ ታሪካቸው ፊልም ሆኖ የሆሊውድን ገበያ እንደሚያጨናንቅ ፈፅሞ አስቦ አያውቅም ።
....
አደለም ታዳጊ ልጅ ይዞ ፡ ለብቻም ቢሆን በሳንፍራንሲስኮ ጎዳና ለአንድ አመት ያህል ቤት አልባ ሆኖ መኖር ከባድ ነው ።
እና ሰው መተላለፍ ሳይጀምር ቀደም ብሎ ይነሳና አቧራውን አራግፎ ታዳጊ ልጁን ወደሚጠብቁለት ዴይኬር ይወስደውና አክስዮን የሚገዙ ሰወችን ሲያስስ ይውላል ፡ ክሪስ ጋርድነር ቀኑን ሙሉ ሲዞር ውሎ ከቤተክርስቲያኖችና ከተለያዩ የእርዳታ ተቋማት በሚያገኛት ገንዘብ ከልጁ ጋር ርካሽ ምግቦችን እየተመገቡ ኑሮን ለማሸነፍ መጣራቸውን ቀጠሉ ።
....
በዚህ ሁኔታ ለአንድ አመት ያህል ከሰራ በኋላ ፡ ከፍተኛ ሽያጭ በማስመዝገቡና ፡ የማለፊያ ፈተናውን በጥሩ ውጤት በማለፉ ከለማጅ የአክስዮን ሽያጭ ሰራተኝነት በእድገት ዋና የሽያጭ ሰራተኛ ሆነ ።
...
አሁን ቤት መከራየት ይችላል ። ጋርድነርና ልጁ ከጎዳና ህይወት ወጡ ልጁን ጥሩ ትምህርት ቤት አስገባው ብዙም ሳይቆይ Gardner Rich &co የተባለውን የአክስዮን ሽያጭ ካምፓኒ ከፈተ ።
.....
ከዛ ሁሉ ፈተና በኋላ ያ ሁሉ የችግርና መከራ ጊዜ አልፎ ጋርድነርና ልጁ በምቾት መኖር ጀመሩ ።
.....
ከአመታት በኋላ ዛሬ ላይ ክሪስ ጋርድነር 165 ሚሊዮን ዶላር ሀብት ያለው ሰው ሲሆን ልጁም የሱን ፈለግ ተከትሎ የተሳካለት ቢዝነስ ማን ሆኗል ።
.....
እንግዲህ ይህ የክርስቶፎር ጋርድነርና የክሪስ ጁንየር ታሪክ ነው The Pursuit of Happyness በሚል ርእስ ወደፊልም የተለወጠው ።
.....
55 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦለት በዊልስሚዝ መሪ ተዋናይነት የተሰራው ይህ ፊልም በአለም ዙሪያ የምንጊዜም ምርጥ ፊልሞች በሚል ተወዳጅ ፊልሞች ዝርዝር ውስጥ የሚገኝ በእውነተኛ ታሪክ ዙሪያ የተሰራ ፊልም ነው ።
....
የዚህ ሁሉ ታሪክ ባለቤት የሆነው ክሪስቶፎር ጋርድነር አሁን ላይ እራሱን ጡረታ አውጥቶ በአመት 200 ቀናት በተለያዩ ሀገራት እየተጓዘ የህይወት ልምዱን ያካፍላል ።
በሰብአዊ በጎ አድራጎትም የተለያዩ ድርጅቶች ከፍቶ እንደሱ በችግር ውስጥ የሚያልፉ ሰወችን ያግዛል ።
👉በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።
📱ቴሌግራም👉 @Beleqe_boostup
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup