መርሳት... 📖✨
"የማብድ ቢመስለኝ፣ ድንገት አንቺን ሳጣ
አረቄ ቤት ሔጄ፣ አረቄ ስጠጣ
አንድ ግጥም ሰማሁ...
ፍቅርሽን ከልቤ፣ ነቅሎ የሚያወጣ፡፡
ያውም 'መንገድ' በሚል...
ለመንገደኛ ሰው፣ ሰካራም የፃፈው
እዛ ጋ ቁጭ ብሎ...
'ከዳችኝ' እያለ፣ የሚለፈልፈው
'መንገድ' የሚል ግጥሙ፣ ጆሮዬን ገረፈው፡፡
ጆሮዬ ሲገረፍ፣
ጠባሳ ጣለብኝ፣ ግጥሙን እንዳልረሳ
'መንገድ አያደርስም
መንገድ አይመልስም፣ እግር ካልተነሳ❕'
እያለ ይገጥማል...
ደጋግሞ ደጋግሞ፣ ሌላ አይናገርም
እሱም ልክ እንደኔ...
አንዷን በመሔዷ፣ ሳያጣት አይቀርም፡፡
ብቻ ሰክሪያለሁ...
ለመንገደኛ ሴት፣ የተፃፈ ግጥምን፣ ጆሮዬ ያደሞጣል
መሔድሽን ያየ፣ እንደሌለሽኝ ሲያውቅ፣ ሊኖረኝ ይመጣል
ይህ ነው መንገድ ማለት❕
የሰካራም ግጥምን ሰክሬ ስረዳው
ማፍቀር ሳይሆን ለኔ፣ መርሳት ነው ሚጎዳው❕
በቃ ረስተሽኛል❕" 💔
እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕
ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈
"የማብድ ቢመስለኝ፣ ድንገት አንቺን ሳጣ
አረቄ ቤት ሔጄ፣ አረቄ ስጠጣ
አንድ ግጥም ሰማሁ...
ፍቅርሽን ከልቤ፣ ነቅሎ የሚያወጣ፡፡
ያውም 'መንገድ' በሚል...
ለመንገደኛ ሰው፣ ሰካራም የፃፈው
እዛ ጋ ቁጭ ብሎ...
'ከዳችኝ' እያለ፣ የሚለፈልፈው
'መንገድ' የሚል ግጥሙ፣ ጆሮዬን ገረፈው፡፡
ጆሮዬ ሲገረፍ፣
ጠባሳ ጣለብኝ፣ ግጥሙን እንዳልረሳ
'መንገድ አያደርስም
መንገድ አይመልስም፣ እግር ካልተነሳ❕'
እያለ ይገጥማል...
ደጋግሞ ደጋግሞ፣ ሌላ አይናገርም
እሱም ልክ እንደኔ...
አንዷን በመሔዷ፣ ሳያጣት አይቀርም፡፡
ብቻ ሰክሪያለሁ...
ለመንገደኛ ሴት፣ የተፃፈ ግጥምን፣ ጆሮዬ ያደሞጣል
መሔድሽን ያየ፣ እንደሌለሽኝ ሲያውቅ፣ ሊኖረኝ ይመጣል
ይህ ነው መንገድ ማለት❕
የሰካራም ግጥምን ሰክሬ ስረዳው
ማፍቀር ሳይሆን ለኔ፣ መርሳት ነው ሚጎዳው❕
በቃ ረስተሽኛል❕" 💔
እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕
ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈