ፈውስ የራቀው ሰው... 📖✨
አለን ኤስ በአንድ ትልቅ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ድርጅት ውስጥ የመስክ ተወካይ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ ሰው ባለቤትና አራት ልጆች ያሉት ቢሆንም ከሌላ ሴት ጋር ድብቅ የፍቅር ግንኙነት መስርቷል።
ወደ እኔ ሲመጣ ፊቱ ላይ ፍርሃት ይነበብበት ነበር፤ ቁጣ ቁጣም ይለዋል።
የእንቅልፍ እንክብል ካልወሰደ እንቅልፍ በዓይኑ አይዞርም።
ከፍተኛ የደም ግፊት እና ሐኪሙ ያላወቀለት ሌሎች የውስጥ ሕመሞች ነበሩበት።
በዚያ ላይ ከልክ በላይ ይጠጣል።
ብዙም ሳይቆይ ለመረዳት እንደቻልኩት፣ ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤው በውስጡ ያለ ስር የሰደደ የኃጢያተኝነት ስሜት ነው።
ያደገበትን ሃይማኖቱን እጅግ በጣም ያከብራል፣ ይፈራል።
በዚህ የተነሳ የጋብቻ ቃል-ኪዳኑን በማፍረሱ ውስጡ በወንጀለኛነት ስሜት እየተለበለበ ነበር።
ይህንን የአዕምሮ ቁስል እንዲጠግግ እና ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ብሎ አዘውትሮ የሚወስደው መጠጥ ችግሩን ከማባባስ በቀር የፌደለት ነገር አልነበረም።
ነገሩ እሳትን በቤንዚን ለማጥፋት እንደመሞከር ነው።
ይህ ሰው ለምን ፈውስ ራቀው⚡️
አለን ስለ አዕምሮአችን ገለፃ ሳደርግለት በሚገባ አዳመጠኝ።
ችግሩንም ረጋ ብሎ አሰበው።
በመጨረሻ ድብቅ ግንኙነቱን ለማቆም ውሳኔ ላይ ደረሰ።
የመጠጥ ሱሱም ቢሆን ሳይረዳ ከራሱ ለመሸሽ ያደረገው ሙከራ እንደሆነ ተረዳ።
ድብቅ አዕምሮው ውስጥ የተሰነቀረው ችግር ላንዴና ለመጨረሻ ተመንግሎ እስካልወጣ ድረስ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያገኝ ሲገነዘብ፣ በውስጡ የመተማመን መንፈስ ፈጠረለት።
በመጨረሻም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ለመላቀቅ ቻለ።
💡
ከጽሑፉ የምንወስደው ትምህርት፦ከተጠናወተን ጎጂ ልማድ ለመላቀቅ ጥልቅ ፍላጎት ካለን፣ 51% ፈውስ እንዳገኘን ይቆጠራል።
ይህን ጎጂ ልማድ ለማቆም ያለን ፍላጎት ለመቀጠል ካለን ፍላጎት የበለጠ ከሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ከችግሩ መላቀቅ አይከብደንም።
በአዕምሯችን መላልሰን የምናስበው ነገር የመጉላት ባህርይ አለው፤ በመሆኑም፦
• ከጎጂ ልማድ የመላቀቅን ነፃነትና የአዕምሮ ሰላምን መላልሰን እናስብ።
• አትኩሮታችንን ሁልጊዜ በዚህ አዲስ አቅጣጫ እናድርግ።
• ይህን ስናደርግ ቀስ በቀስ የነፃነትና የሰላም ስሜት በመላ አካላችን እየተሰማን ይመጣል።
✍️
ጆሴፍ ማርፊ (Joseph Murphy)📖
"አእምሮን በብቃት በመጠቀም መልካም ሕይወትን የመምራት ቁልፍ ምስጢራት" (ትርጉም፦ እስክንድር ስዩም)
ብሩህና የአእምሮ ሰላም የሞላበት አዲስ ቀን ይሁንላችሁ❕ 🌸📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨📚
ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡ 👇👇👇
🔗
BookMereja.t.me🔗
BookMereja.t.me🔗
BookMereja.t.me