እናስተዋውቅዎ!
ውድ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችን ተከታዮች በዛሬው የእናስተዋውቅዎ ፕሮግራማችን በኢንዱስትሪ ፋይናንሲንግ ክላስተር ስር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች መካከል አንዱ የሆነውን የማዕድን ኢነርጂና ኮንስትራክሽን ዳይሬክቶሬትን እናስተዋውቃችኋለን፡፡ መረጃውን ከክፍሉ ዳይሬክተር ዘቢደሩ ደበበ ወስደናል፡፡
የማዕድን ኢነርጂና ኮንስትራክሽን ዳይሬክቶሬት /mining, energy and construction Directorate/ የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት በማዕድን ማውጣት፣ ማቀናበርና ለገበያ ማቅረብ ናቸው፡፡
ለምሳሌ
- ወርቅ፣ ኮፐር፣ አይረን፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት የሆኑ እንደ ሲሚንቶ፣ ሴራሚክ፣ ግራናይት፣ ማርብል፣ ላይምስቶን የመሳሰሉትን በሚያመርቱ ፕሮጀክቶች ላይ ለተሰማሩ ባለሃብቶች በባንኩ ፖሊሲና መመሪያ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ማሟላታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ብድር የሚያመቻች ክፍል ነው፡፡
ክፍሉ ደንበኞች የጠየቁትን የብድር ጥያቄ ከመመለስ ባለፈ የወሰዱት ብድር ለሚፈለገው ዓላማ ስለመዋሉ ለማረጋገጥ እንዲሁም በተሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ የማማከር፣ የክትትል እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የቴክኒክ ድጋፎች እንዲያገኙ የማድረግ ተግባራትም ያከናውናል፡፡
ከባንኩ የብድር አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ ደንበኞች ለስራ ዝግጁ ሆነው፣ የሚሰማሩበትን ዘርፍ መርጠው፣ ማሟላት የሚጠበቅባቸውን በባንኩ በዝርዝር የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው፣ እስከመጡ ድረስ ባንኩ የሚያቀርበውን የብድር አገልግሎት ለማመቻቸት ክፍሉ ዝግጁ ነው፡፡
ይህ የስራ ክፍል ከሌሎች ክፍሎች ለየት የሚያደርገው በአብዛኛው ግዙፍ የሆኑ ፕሮጀክቶች የሚስተናገዱበት ክፍል መሆኑ ሲሆን፣ በተለይ በማዕድን ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ደንበኞች በዝርዝር ከሚጠየቁት መስፈርቶች በተጨማሪ mining licensee እንዲያቀርቡ የሚጠየቅ በመሆኑ የሚጠበቅባቸው አሟልተው ቢመጡ የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!