ከተመሰረተ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መንግስት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች የመካከለኛ እና ረጅም ጊዜ የልማት ፋይናንስ ለማቅረብ የተቋቋመ ብቸኛ የፖሊሲ ባንክ ነው።
ባንኩ በተለያዩ የስኬት እና የፈተና ጊዜያትን አልፎ ዛሬ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ አንጋፋነቱን በሚመጥን ዓይነት ቁመና ላይ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ እንደመሆኑ መጠን የንግድ ባንኮች በፋይናንስ ተደራሽ በማይሆኑባቸውና በረጅም ጊዜ ሂደት ለአገር ኢኮኖሚያዊ ልማት አቅም ሊሆኑ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ ይታወቃል፡፡ ባንኩ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለኢንዱስትሪ ሽግግር የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ያለ ባንክ ነው::
ባንኩ መንግሥት አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን ያግዛሉ፤ ኢኮኖሚያዊ ልማት ያረጋግጣሉ በሚል ቅድሚያ ትኩረት በሰጣቸው የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ብድር በማቅረብ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የአገራችንን ልማት እያፋጠነ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡ በዚህም ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት ባለፉት ጥቂት አመታት ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ሥራ ያካሄደ ሲሆን በበርካታ የፋይናንስ መለኪያዎች ለውጦችንና ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኢትዮጵያውያን ሃብት በመሆኑ የተለወጠ ኢኮኖሚ ያላት አገርና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሩ ጤናማ ብሎም መሰረታዊ ኑሮው የተለወጠ ማህበረሰብን ለመፍጠር በመስራት ላይ ነው፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግም ባንኩ ፋይናንስ የሚያደርጋቸው ፕሮጀክቶች አገርንና ህዝብን መለወጥ የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ለግዢ ይውል የነበረን የውጭ ምንዛሬ ማስቀርት የሚችሉ እና ምርቶቻቸውን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬም ጭምር ማስገኘት የሚችሉ ፕሮጀክቶች በመሆናቸው በረጅም ጊዜ ሂደት የሚፈጥሩት በጎ ተጽእኖ የአገርን ኢኮኖሚ በማሻገር ሂደት የራሳቸውን ሚና ይወጣሉ፡፡
ባንኩ ግብርና እና ኢንዱስትሪ ያላቸውን የእርስ በእርስ መስተጋብር ያገናዘበ የፋይናንስ ድጋፍ ነው የሚያደርገው፡፡ ግብርና ለኢንዱስትሪ፤ ኢንዱስትሪም ለግብርና አስፈላጊና ተመጋጋቢ ናቸው፡፡ የአገራችን ኢኮኖሚ የግብርና ግብዓቶችን ተጠቅመው በአገር ውስጥ ያለውን የገበያ ፍላጎት ማሟላት እና እሴት ተጨምሮባቸው ወደ ውጭ የሚላኩ የኢንዱስትሪ ምርቶች በብዛት እንዲመረቱ የሚያበረታታ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ይህን የመንግስት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የአምራች ዘርፉን እድገት ለማፋጠን ፋይናንስ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም ባለፉት ዓመታት የጨርቃጨርቅ፣ የእንጨት ስራዎች፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ የዱቄት፣ የዶሮ እርባታ፣ የቡና እና መሰል የአገር ውስጥ ገበያ ፍላጎትን የሚያሟሉ እና ለዓለም ገበያ መቅረብ የሚችሉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ፋይናንስ ያደረገ ሲሆን ባንኩ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት ጥረት ማድረጉን በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!