ዳሸን ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ በተከፈተው ኢሬቻ ባዛርና ኤግዚቢሽን ላይ አዳዲስ አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል
ኢሬቻ ባዛርና ኤግዚቢሽን በዛሬው ዕለት በኤግዚቢሽን ማእከል በይፋ ተከፍቷል።
የዳሸን ባንክ መልካ ገፈርሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳለ ይገዙ ዳሸን ባንክ ዛሬ በይፋ በተከፈተው ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ አገልግሎት እየሰጠና እያስተዋወቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ በርካታ ተሳታፊዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለጎብኝዎች ያቀረቡ እንደመሆናቸው በዳሸን ባንክ የዲጅታል የክፍያ አማራጮች በኩል ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲሸጡ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
ባንኩ "ሾፐርስ ኤንድ ትራቭለርስ" ክለብ ካርዶች፣ "አሁን ይብረሩ ቆየት ብለው ይክፈሉ "(Fly Now Pay Later)፣ "ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ" እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን እያስተዋወቀ ይገኛል።
የኤግዚቢሽንና ባዛሩ አዘጋጅ ሐገሬ ኤቨንት ኤንድ ፕሮሞሽን ማርኬቲንግ ማናጀር ሳምራዊት ካሳሁን በበኩላቸው ከዛሬ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆየውን ይህን ባዛርና ኤግዚቢሽን ከ2መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ ከውጭ ሃገር ኢሬቻን ለማክበር የሚመጡ የዲያስፓራው ማህበረሰብ አባላትና ከሃገር ውስጥ ከተለያዩ አካባቢዎችየሚመጡ ጎብኝዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑም አስረድተዋል ።
በባዛርና ኤግዚቢሽኑ ላይ ከ200 በላይ ነጋዴዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው የቀረቡ ሲሆን ዳሸን ባንክ ያቀረባቸው ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎቶች ሸማችና ነጋዴው በቀላሉ እንዲገናኙ ያግዛል።
በተጨማሪም ባንኩ ገንዘብ የመሰብሰብና ጨምሮ ሌሎች የባንክ አገልግሎቶችን በባዛርና ኤግዚቢሽኑ ላይ እየሰጠ ይገኛል።