"ዳሸን ባንክን የመሰሉ የሩጫው አጋር ተቋማት ስለሚያደርጉት ትብብር እናመሰግናለን " - አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ
ዳሸን ባንክ ብቸኛ የባንክ አጋር የሆነበት ታላቁ ሩጫ የፊታችን ዕሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
በዛሬው እለት ሰለ ሁነቱ ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራአስኪያጅ ዳግማዊት አማረ የፊታችን ዕሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ አብሮነትን የምናሳይበት ነው ብለዋል።
ዳሸን ባንክን የመሰሉ ድርጅቶች የሁነቱ ስፓንሰር ብቻ ሳይሆኑ አጋር ናቸው ብለዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው ታላቁ ሩጫ ኢትዮጵያ ሃገራችን የአትሌቲክስ ምንጭ መሆኗን የምናሳይበት ነው ብለዋል።
ታላላቅ ሯጮቻችንን የምናመሰግንበት መድረክ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ሃገራችን ያላትን የቱሪዝም ስፍራዎች የምናስተዋውቅበትና የስፓርት ቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት የሚያግዝ እንደሆነም አብራርተዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ ዳሸን ባንክን የመሰሉ የሩጫው አጋር ተቋማት ስለሚያደርጉት ትብብር ምስጋና አቅርቧል።
ዳሸን ላለፉት 4 አመታት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተመራጭ የክፍያ አጋር ሆኖ የዘለቀ ሲሆን በዘንድሮዉም ሩጫ ላይ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
ባንኩ ከዚህ ቀደም በክልል ከተሞች የተዘጋጁ ሩጫዎችን ስፓንሰር በማድረግና የቲሸርት ሽያጭ በባንኩ የክፍያ አማራጮች እንዲፈጸሙ በማስቻል በአጋርነት ዘልቋል፡፡
ዳሸን ባንክ ከሚሰጣቸው የባንክ አገልግሎቶች ባሻገር ማህበረሰቡ ጤናውን እንዲጠብቅና የአብሮነት ትስስሩ እንዲያድግ መሰል የስፓርት መርሃ ግብሮችን እየደገፈ ይገኛል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጅ ዋና ኦፊሰር አቶ ኤልያስ ሁሴን ታድመዋል፡፡