ዳሸን ባንክ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮምሽን (ECA) በተዘጋጀ ባዛር ላይ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል
የባንኩ አምስት ቅርንጫፎች በባዛሩ ላይ የተሳተፉ ሲሆን ሙሉ የባንክ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
በዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የተቋቋመው ህብረት (Diplomatic Spouses Grpup Ethiopia) የተዘጋጀው ይህ ባዛር ለምግብነት የሚውሉ ሸቀጦች ፣አልባሳት ፣የመዋቢያ ቁሳቁሶችና ሌሎች ሸቀጦች ለገበያ ቀርበውበታል።
በዳሸን ባንክ ግዮን ቅርንጫፍ ኮርፓሬት ማዕከል ስራአስኪያጅ አጀብወርቅ አሊ በባዛሩ ላይ የሚከናወኑ ግብይቶች በባንኩ የአገልግሎት አማራጮች እንዲፈጸሙ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
የባዛሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ባዛሩ የእርስበርስ ትውውቅን ለማጠናከርና የባህል ትስስር እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።ከባዛሩ የሚገኘው ገቢ ለበጎአድራጎት ስራ የሚውል እንደመሆኑ ሁነቱ ደስ የሚል ድባብ እንዳለው ተናግረዋል ።
ዳሸን ባንክ አጋር የሆነበት ይህ ዲፕሎማቲክ ባዛር ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ነው።