#በእመቤታችን ቅ/ ድንግል ማርያም ፊት የሚደረግ ጸሎት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የጸጋ ግምጃ ቤት ምዕራገ ጸሎት ወላዲተ አምላክ እመቤቴ ሆይ የምሕረት ምልጃሽ ፈጥኖ ይደረግልኝ። በኃጢአት ለተያዝኩት ለእኔ ለልጅሽ መጽናናትንና መፈወስን ከሥዕልሽ ፊት ልስማ። የእናትነት በረከትሽ ከዚህ ሥዕል ፊት ይውጣ።
እኔ ባርያሽ በዚህ ሥዕል ፊት ቆሜ እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሰላም ላንቺ ይሁን ብዬ እጅ እነሳለሁ። እንደ አባ ሕርያቆስም በምንና በምን እመስልሻለሁ ብዬ አድናቆቴን እገልጣለሁ ። እንደ ቅዱስ ያሬድም ለመድኃኒት እናት ክብር ይገባታል እላለሁ።
እናቴ ሆይ በመግባቴም በመውጣቴም በጉዞዬ ሁሉ አትለይኝ በዚህ ሥፍራ ባለው ሥዕልሽ ፊት ተማጽኖዬን እንዳደረስኩ በጽርሐ አርያም ባለው የልጅሽ ዙፋን ፊት የእናትነት በረከትሽ ለእኔ ለኃጢአተኛው ልጅሽ ይድረስ።
የመስቀል ስር ስጦታዬ የመዳን ምክንያት ምልክቴ፤ ወላጅ እንደሌለው ልጅ አትተይኝ፣ ለመዳኔ ማንን እጠራለሁ ለፈውሴስ ማንን እጠጋለሁ ልጅሽን አይደለምን፤ ከአንች ምልጃስ በቀር ለእኔ የሚከራከር ማን ነው ንጽሕት ሆይ ከእርኩሰቴ ሁሉ ነጻ አድርጊኝ ለዘለዓለሙ አሜን።
#ከጸሎተ ጽሞና የተወሰደ
@Deaconchernet