#የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ያከናወንክ፣ የሁሉ ፈጣሪ፥ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፣ እልፍ አእላፋት መላእክት የሚያመሰግንህ፣ ትእልፊተ አእላፋት ሊቃነ መላእክት የሚገዙልህ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆኑ ኪሩቤል የሚቀድሱህ ክንፋቸው ስድስት የሆኑ ሱራፌል ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅድስናን የሚቀድስ፣ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ፣ የነገስታት ንጉሥ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፣ ብርሃናትን የተጎናጸፈ እያሉ የሚያመሰግኑህ፤ አንተ ወደህ ፈቅደህ ልጅህን ከአተ ዘንድ ወደ እኛ ላክኸው፤ እርሱም ቃልህ ነው።
የጠፉትን የሚናገሩ በጎች የሚባሉ የሰው ልጆችን ወደ አንተ ይመልሳቸው ዘንድ። እንደ ፈቀደ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ከሰማያት ወረደ። ከቅድስት ድንግል ማርያምም ሰው ሆነ። ይህንን ሁሉ ያደረግኸው ለሰው ልጆች መድኀኒት ይሆን ዘንድ ነው። ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣኸን፤ አንተን ወደማወቅም መራኸን፤ አቤቱ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ መድኀኒታችን ለመሆን ሰው በሆነ በዋህድ ልጅህ፤ እነሆ ጌታ ይህ ዐመፀኛ ከሐዲ በሙሽራህ ላይ ያደረገውን ተመልክተሃል።
የቤተ ክርስቲያንህን ልጆች እንደያዛቸውና እንደ በግና ፍየል እንዳረዳቸው። የሕዝብህንና የርስትህን ልጆችም እንዳጠፋቸው። ስለ ወንድሞቼ ስለ ምእመናን ቀንቻለሁና በመሲሕ መስቀል ኀይል ይህን የእኛንና የአንተን ጠላት እወጋው ዘንድ እወጣለሁ። እነሆ እኔ በአንተ እና በዋህድ ልጅህ፣ አመንኩ በመሠዊያው ቀንድም ተማጸንኩ በሃይማኖትህም ጸናሁ።
ስለዚህም ስምህን የሚያውቁ አምላካቸው ወዴት አለ እንዳይሉኝ ከተስፋዬ አታሳፍረኝ። በብዙ አበሳየና ኃጢአት ምክንያት ጸሎቴን ባትሰማኝ ስእለቴንም ብትተዋት እንኳን አቤቱ በዚህች ሀገር ግደለኝ እንጂ ስምህን ለማያውቁ ከሐዲ ጠላቶችህ ርስትህን አታሳልፋት። እኛ ሕዝቦችህ የመንጋህም በጎች ነንና። እስከ አለምም እናመሰግንሃለን።
#እኛም አለማዊ ጌጣችንን፣ የኃጢአት ልብሳችንን አውልቀን፤ ትህትናን ተላብሰን በተሰበረ ልብ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንግባ። ዲያቢሎስ የከፈተብንን ጦርነት ድል እንነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው። ዋናችን ይህን አስተምሮናልና። የእግዚአብሔር ሀይል እንጂ ንግሥናው ይህን እንደማያደርግ አውቋልና፤ ለኛም ባለጸጋነታችን ድልን አያደርግም።
#ኢትዮጵያንም እንደ ጥንቱ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍበትን ዘመን ያምጣልን። አሜን።
ምንጭ: የናግራን ሰማዕታት