ሉሲዎቹ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል !
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከዩጋንዳ አቻው ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በመለያ ምት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል።
የመልስ ጨዋታውን አበበ ቢቂላ ስታዲየም ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ በመደበኛ ሰዓት ጨዋታውን 2ለ0 አሸንፏል።
የሉሲዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አረጋሽ ካልሳ እና እፀገነት ግርማ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በድምር ውጤት 2ለ2 መሆናቸውን ተከትሎ በተሰጠ የመለያ ምት ሉሲዎቹ 5ለ4 አሸናፊ ሆነዋል።
ሉሲዎቹ በሁለተኛው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ከታንዛኒያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ አሸናፊ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe