TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Dr. Eyob Mamo

15 Sep, 05:02

Open in Telegram Share Report

የአዲስ ዓመት ጅማሬ ! (ክፍል ሁለት)

ከትክክለኛ ሰዎችና ነገሮች ጋር የመተሳሰር መርሆዎች!

በያዝነው አዲስ ዓመት፣ የተሻለ ግንኙነት ለመመስረት ወስኑ! ባለፈው ዓመት የነበራችሁን ጎጂ ግንኙነት ስታቆሙ፣ ውስጣችሁ ባዶነት ሊሰማው መቻሉ ተፈጥሯዊ ሂደት ነውና ተቀበሉት፡፡

የተዋችሁትና ከውስጣችሁ ያስወጣችሁት ነገር ይዞት የነበረው ቦታ ባዶ ስለሚሆን ከትክክለኛ ሰዎች ጋር ጤናማ ግንኙነትን የመመስረትን እና አዳዲስና ጤናማ ሁኔታዎችን የመልመድ ጉዙ ጀምሩ፡፡

ይህንን አድርጉ . . .

1. የሚያሳድጓችሁን ሰዎች ምረጡ

ሰዎች ስለቀረቧችሁ ብቻ አትቅረቡ፣ ትኩረት ስለሰጧችሁ ብቻ ራሳችሁን ክፍት አታድርጉ፡፡ ከዓላማችሁ እና ለማደግ ከምትፈልጉት ከፈታ አንጻር እድገትን፣ ጥበብንና መልካም ባህሪን የሚያበረታቱ ሰዎችን ቅረቡ።

2. ለአስፈላጊው ነገር ቁርጠኛ ሁኑ

ከአንድ ነገር ተለይቶ ወደ ሌላ ነገር መጓዝ ቁርጠኝነት ይፈልጋል፡፡ ጊዜያችሁንና ኃይላችሁን ለዓላማችሁና ቅድሚያ ለምትሰጡት ነገሮች ስጡ እንጂ ለጊዜው ጥሩ ስሜት የሰጣችሁን ነገር ብቻ አትከተሉ፡፡

3. መልካሙን ልምምድ አሳድጉ

በተፈጥሮ ሂደት ውስጥ ከጥሩ ዘር ይልቅ አረም በቀላሉ ይበቅላል፡፡ በሕይወታችሁም እንዲሁ ነው፡፡ ጥሩ ግንኙነትና ጥሩ ልማድ ሆን ተብሎ በተከታታይ በሚደረግ ጥረት ነው የሚያድጉትና ጊዜ ስጡት።

ይቀጥላል . . .

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
https://t.me/Dreyob

12.1k 0 54 1 128
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot