TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Dr. Eyob Mamo

4 Oct, 09:22

Open in Telegram Share Report

ሰላም ይሁንላችሁ!

ከሁሉም በፊት ከፈጣሪችን ጋር በመስማማት የመኖራችን አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆነ፣ ሰላም ማለት ችግር አለመኖር ሳይሆን፣ በችግር መካከልም ብንሆን የተረጋጋ አእምሮ መያዝ ነው።

ችግሮች፣ ጫናዎች፣ አለመግባባቶች፣ ውድቀቶችና እርግጠኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች በሕይወታችን ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ። ሰላም ግን እነዚህ ችግሮች ቢኖሩም አእምሯችንን በመቆጣጠር፣ ተስፋችንን በመጠበቅና በተረጋጋ መንፈስ ሁኔታውን መጋፈጥ ነው።

1. ሰላም ማለት ችግር አለመኖር አይደለም
ሁሉም ሰው በሕይወቱ ውስጥ ችግር ያጋጥመዋል። ሰላማችን ችግር ባለመኖሩ ላይ ብቻ ከተመሠረተ፣ በሕይወታችን ውስጥ ብዙ ጊዜ ሰላም ማግኘት እንቸገራለን።

2. ሰላም የሁኔታው ሳይሆን የምላሽ ጉዳይ ነው
ሁለት ሰዎች ተመሳሳይ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል። አንዱ በጣም ሊደነግጥና ተስፋ ሊቆርጥ ይችላል፤ ሌላው ግን፣ “ይህ ከባድ ነው፣ ግን ቀስ በቀስ እጋፈጠዋለሁ” ብሎ ሊረጋጋ ይችላል። ሁኔታው አንድ ነው፤ የአእምሮ ምላሻቸው ግን የተለያየ ነው።

3. ሰላም የምንቆጣጠረውንና የማንቆጣጠረውን ማወቅ ነው
የሰላም ምስጢር የገባው ሰው ከአቅሙ በላይ ያሉ ነገሮችን ለመቆጣጠር ኃይሉን ሁሉ አያጠፋም። በሚችለው ነገር ላይ ይሠራል፤ መቆጣጠር የማይችለውን ደግሞ መተውን ይማራል።

የሰላም እሁድ ይሁንላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

1.9k 0 8 2 40
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot