የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን አውሮፕላን ተረከበ
*************************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤር ባስ A350-1000 አውሮፕላን ተረክቧል፡፡
በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲ ለሚክ፣ የኤር ባስ ኩባንያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት አውሮፕላኑ በአየር መንገዱ ምድረ ቀደምት (Ethiopia land of origins) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው A350-1000 አውሮፕላን 400 መቀመጫዎች አሉት፡፡
አየር መንገዱ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዝ 25 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየሰራ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍ እና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ አየር መንገዱ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን መናገራቸው ይታወሳል፡፡