በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ
******************
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ በተጀመረው መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድ የኢኮኖሚና መሰረተ ልማት ዘርፍ አማካሪ ምትኩ በድሩ (ዶ/ር ኢ/ር) እንደገለጹት፤ በየዓመቱ የሚከናወነው የተፋሰስ ልማት ሥራ በክልሉ ውጤታማ እየሆነ ይገኛል ብለዋል።
ክልላዊ የተፈጥሮ ሀብት ሽፋን በየጊዜው እንዲጎለብት የተፋሰስ ልማት ሥራው አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
ውጤቱን ቀጣይ ለማድረግ እና የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የካፋ ዞን ምክትል አስተዳደርና ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ንጉስ ከዚህ ቀደም በለሙ ተፋሰሶች አርሶ አደሮች የሥነ ሕይወታዊ ሥራዎችን በማከናወን ተጠቃሚ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል።https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0e9g1NNm1kcszc7SoAajLrnsbHyuYWMsRCFTSdhm8q2ipdnVon1qgKTLSNCWzFGa2l