አሜሪካ ያለባት ዕዳ 36.2 ትሪሊዮን ዶላር ደረሰ
***
የአሜሪካ መንግስት ያለበት ዕዳ 36.2 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ከአሜሪካ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) አንፃር 122 በመቶ ሆኗል።
የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳ በየሦስት ወሩ በ1 ትሪሊዮን ዶላር ይጨምራል።
ከ36.2 ትሪሊዮን ዶላሩ የአሜሪካ ዕዳ ውስጥ ሦስት አራተኛው ከሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የቀረበ ሲሆን፤ ባለሃብቱ ዋረን ቡፌት የ314 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸውን የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሰነዶችን ይዘዋል።
አሜሪካ ካለባት ብድር ውስጥ 9.05 ትሪሊዮን ዶላሩን የያዙት ከአሜሪካ ውጪ ያሉ አካላት መሆናቸው አልጃዚራ ዘግቧል። ከዚህ ውስጥ የጃፓን፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የቻይና ባለሃብቶችና ተቋማት ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል።
የአሜሪካ ዕዳ 36.2 ትሪሊዮን ዶላር እንዴት ደረሰ?
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ