የኮርፖሬሽኑ የምገባ ማዕከል ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ
----------------------
የገና በአልን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የተስፋ ብርሃን ምገባ ማእከል ተጠቃሚዎች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ፡፡
በኮርፖሬሽኑ የማህበራዊ ጉዳዮችና የሥራ ቦታ ደህንነት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ቁምላቸው በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ128 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር፣ በድምሩ 640 ሺህ ብር ለግሷል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 09 የሚገኘው የምገባ ማዕከሉ ከሰኔ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለበርካታ ወገኖች የምገባ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡