የውስጥ ባለድርሻ አካላት ፎረም በተለያዩ የአሰራር ማኑዋሎች ላይ ተወያየ
----------
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የውስጥ ባለድርሻ አካላት ፎረም በተለያዩ የአሰራር ማንዋሎች ላይ ጥልቅ ውይይት አደረገ፡፡
የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ከሲቶ የማኑዋሎች ዋና ዓላማ የኮርፖሬሽኑን መብት እና ፍላጎት ማስጠበቅ እና የተቋሙን መልካም ስምና ዝና በዘላቂነት ጠብቆ ማቆየት ነው ካሉ በኋላ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ክፍሎች ማኑዋሎችን ሙሉ በሙሉ መተግበር ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
እስከ አሁን የስጋት ሥራ አመራር፣ የይገባኛል ሥራ አመራር፣ የተሰብሳቢ ሂሳብ ሥራ አመራር፣ የሥራ ውል ሥራ አመራር እና የክርክር ጉዳዮች ሥራ አመራር ማኑዋሎች በጥንቃቄ ተቀርጸው ለሥራ ዝግጁ ሆነዋል፡፡
ፎረሙ በየወሩ በመሰብሰብ በስጋት፣ በይገባኛል እና ህግ-ነክ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የሚወያይ አደረጃጀት ነው፡፡