በጥራት ሽልማት ድርጅት የልህቀት ሞዴል መሠረት ምዘና እየተካሄደ ነው
-----------
በኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ልህቀት ሞዴል መሠረት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ምዘና (assessment) እየተካሄደ ነው፡፡
የኮርፖሬሽኑን የልህቀት ጉዞ ለማሳካት እንዲያግዝ ለኮርፖሬሽኑ የሥራ ክፍሎች በልህቀት ሞዴሉ ላይ ቀደም ሲል ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን በዚሁ መሠረት በሃብት አያያዝ (resource management) እና የፕሮጀክት አመራር (project management) ላይ ትኩረት በማድረግ በሥራ ክፍሎች በመገኘት የመገምገምና የመመዘን ሥራ ተከናውኗል፡፡ በቀጣይ ሳምንት ሌሎች የሥራ ክፍሎች እንደሚመዘኑ የትራንስፎርሜሽን ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት ያስታወቀ ሲሆን ለምዘናው ቀደም ብሎ የተላከውን የምዘና ቼክ ሊስት መሠረተ አድርገው መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡