TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
EEP Communication

22 Aug, 14:54

Open in Telegram Share Report

የሀገርን ማዕዘናት በንጹህ ኃይል የማብራት ጉዞ
.....///...... 
ሀገራችን ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን በጥቅም ላይ በማዋል የምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ለመሆን አበክራ እየሰራች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለፁት "የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችንን በስፋት በማሳደግ፣ የሀገራችንን እያንዳንዱን ማዕዘን እያበራን እንገኛለን" የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኤኮኖሚና በኃይል ዘርፍ የያዘችውን ሀገራዊ ራዕይና በተግባር ያሳካቻቸውን ስኬቶች ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
 
ሀገርን በታዳሽ ኃይል ለማብራት ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል፡-
1. የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 5,150 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ግዙፍ የውሃ ኃይል ማመንጫ ሲሆን የሀገሪቱን ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ከእጥፍ በላይ አሳድጓል። ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች፣ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ለዜጎች አስተማማኝ ኃይል ከማቅረቡ ባሻገር ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ ይገኛል።
 
2. የታዳሽ ኃይል ምንጮች አሰባጥሮ መጠቀም                
ኢትዮጵያ እንደሀገር ከውሃ ኃይል ማመንጫዎች በተጨማሪ እንደ አሸጎዳ፣ አዳማ 1 እና 2፣ አይሻ 2 እና አሰላ ያሉ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ መጀመር ከንፋስ የማመንጨት አቅምን 504 ሜጋ ዋት ያደረሱ ናቸው፡፡  ማሳደግ እንዲሁም የአይሻ የንፋስ ኃይል ፕሮጀክትን የመሳሰሉ አዳዲስ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ የኃይል አማራጩን ማሰፋፋት ተችሏል። በአሉቶ ላንጋኖ እና በቱሉ ሞዬ እየተካሄዱ ያሉ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶች የወደፊት የኃይል ዋስትና ስብጥርን ከሚያረጋግጡ የታዳሽ ኃይል አማራጮች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዋናው ግሪድ ርቀው ለሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የፀሐይ ኃይል አነስተኛ ግሪዶችን (Mini-grids) እና የቤት ውስጥ ሶላር ሲስተሞችን መስፋፋት የኃይል ተደራሽነትን lማሳደግ ተዐማሪ አቅም ፈጥሯል፡፡
 
3. የኃይል ተደራሽነትን ማፋጠን
በገጠርና ከከተሞች ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በሺዎች የሚቆጠሩ መንደሮችና አነስተኛ ከተሞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል፡፡ የመኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ጣቢያዎችና የግብርና ምርት ማቀናበሪያዎች ኃይል እንዲያገኙ በማድረግ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ጥራት ማሻሻል ተችሏል።
 
4. ቀጣናዊ የኃይል ትስስር
ኢትዮጵያ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች የሚመነጭ ንፁህ ኢነርጂ ወደ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ በመላክ የኃይል ትስስር ፈጥራለች፡፡
 
5. የግል አልሚዎች ወደ ዘርፉ መግባት


ዘርፉን ለማዘመን በተከናወኑ የፖሊሲ ማሻሻያዎች የሀገር ውስጥና የውጭ የግል አልሚዎች (Private Developers) በኃይል ማመንጨት ሥራ ላይ በር የሚከፍት የፖሊሲ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል።
 
በአጠቃላይ የታዳሽ ኃይል አማራጮችን ማስፋፋት የዜጎችን የዕለት ተዕለት ህይወት ከማሻሻሉም በላይ ሀገራችንን ወደ ተሻለ የኢንዱስትሪ እና የኢኮኖሚ እድገት የሚያሸጋግር የታሪካዊ ጉዞ አወንታዊ ማሳያ ነው።

"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

3.2k 0 0 5
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot