Posts filter


እንኳን ለነቢዩ መሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ!
 
የብርሃን ጉዞ አያከትምም!
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማህበረሰባችንን ህይወት የሚያበራ፣ የአኗኗር ዘይቤ የሚለውጥ፣ የተጀመረውን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የሚያሳልጥና የዲጂታል 2030 ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
 
ከኃይል ማመንጫ ጣቢያዎቻችን የሚመነጨውን ኃይል በሀገሪቱ ሁሉም አቅጣጫ በተዘረጉት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና በማከፋፈያ ጣቢያዎቻችን ጨለማን ገፈን በብርሃን ለመተካት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትጋት እየሰራን እንገኛለን፡፡
 
ለእስልምና እምነት ተከታዮች የመውሊድ በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ ስንመኝ የበዓሉ አስተምህሮ የሆነውን የመተሳሰብ፣ የፍቅርና የመደጋገፍ ብርሃን ለሌሎች እንዲያበራ በጎነትና ትጋትን የዘወትር መመሪያችን በማድረግ ነው፡፡
 
ኢድ ሙባረክ!
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም


የወደቁ የብረት ምሰሶዎችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየተሰራ ነው
....///....
ከለገጣፎ - ቃሊቲ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወደቁ አምስት የብረት ምሰሶዎችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ 1 ሪጅን አስታወቀ።

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደተናገሩት የታወር አካላትን ከተለያዩ ቦታዎች በማሰባሰብ እና ጥገናውን በማከናወን የሁለት ታዎሮችን ተከላ ሥራ ማከናዎን ተችሏል፡፡

ቀሪዎቹ ሶስት የወደቁ የብረት ምሰሶዎች የመሠረት ቁፋሮ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የመሠረት ቁፋሮ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለብረት ምሰሶዎች መሠረት ግንባታ የሚውሉ የአሸዋ፣የጠጠር እና የሲሚንቶ ግብአቶች ሳይት የማድረስ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ነው ዳይሬክተሩ ያስታወቁት፡፡

አምስቱ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ መውደቃቸው ይታወሳል፡፡

"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም


የጣቢያውን የኦፕሬሽን ባለሙያዎች አቅም ለማሳደግ ይሰራል
....///....
በኢትዮ ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ የኦፕሬሽን ሥራዎች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትና የባለሙያዎችን አቅም ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ።

በተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የተመራው የሥራ አመራር ቡድን በኮንቨርተር ጣቢያው እና የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል በሆነው የወላይታ ሶዶ ማከፋፈያ ጣቢያ የመስክ ምልከታ አድርጓል።

የኮንቨርተር የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ግርማ  ስለ ጣቢያው የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራ አስመልክቶ ባደረጉት ገለፃ እስከ ኬኒያ የተዘረጋው 1 ሺ 45 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመር 2 ሺህ ሜጋ ዋት ኃይል የማስተላለፍ አቅም ይዞ 2014 ዓ.ም ላይ ወደ ኦፕሬሽን ገብቷል።‌‎

ተጨማሪ ለማንበብ…
https://www.eep.com.et/?amh-news=የጣቢያውን-የኦፕሬሽን-ባለሙያዎች-አቅም&lang=am

"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም



4 last posts shown.