የወደቁ የብረት ምሰሶዎችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየተሰራ ነው
....///....
ከለገጣፎ - ቃሊቲ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወደቁ አምስት የብረት ምሰሶዎችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ 1 ሪጅን አስታወቀ።
የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደተናገሩት የታወር አካላትን ከተለያዩ ቦታዎች በማሰባሰብ እና ጥገናውን በማከናወን የሁለት ታዎሮችን ተከላ ሥራ ማከናዎን ተችሏል፡፡
ቀሪዎቹ ሶስት የወደቁ የብረት ምሰሶዎች የመሠረት ቁፋሮ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የመሠረት ቁፋሮ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለብረት ምሰሶዎች መሠረት ግንባታ የሚውሉ የአሸዋ፣የጠጠር እና የሲሚንቶ ግብአቶች ሳይት የማድረስ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ነው ዳይሬክተሩ ያስታወቁት፡፡
አምስቱ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ መውደቃቸው ይታወሳል፡፡
"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም