✅ኦፕን ኤ.አይ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት አዳዲስ የኤ.አይ ሥርዓቶችን (ኤጀንቶች) አስተዋወቀ፡፡
📍የመጀመሪያው ኤ.አይ ኤጀንት ለጥናትና ምርምር ስራ አጋዥ እንዲሆን የተሰራ ነዉ፡፡ ዲፕ ሪሰርች የተሰኘው ኤጀንቱ የኦፕን ኤ.አይ ኦ ስሪ ሚኒ (o3-mini) ሞዴልን በመጠቀም በልጽጓል፡፡
📍በጥናትና ምርምር ስራ ዉስጥ ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጀዉ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን አስሶ የተጠናከረ ጽሁፍ ማዘጋጀት ነዉ፡፡ ኤጀንቱ በበይነ መረብ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ጽሁፎችን፣ ምስሎችን እና ሰነዶችን አሰሳ በማድረግ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ትንተና ያዘጋጃል፡፡
📍ዲፕ ሪሰርች በቻት ጂፒቲ ላይ የሚገኝ ሲሆን የካቲት ወር መጨረሻ ላይ አዳዲስ ማሻሻያዎችን በማካተት በመተግበሪያ መልኩ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተነግሯል፡፡
📍ሌላኛዉ ኤ.አይ ኤጀንት ደግሞ ኦፕን ኤ.አይ ኦፕሬተር ይሰኛል፡፡ ኮምፒዩተር ዩዚንግ ኤጀንት (CUA) የተሰኘ አዲስ ሞዴልን በመጠቀም የበለፀገ ነዉ፡፡ ይህ ኤጀንት በበይነ መረብ አሳሾች (ብራውዘር) ላይ በተጠቃሚዎች ፍላጎት መሠረት የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የሚችል ነው፡፡ በዚህም ቅጾችን መሙላት፣ ሸቀጦችን ማዘዝ፣ የሆቴሎች ዋጋ ዝርዝርን ማጥናት እና የተሻለ ዋጋ ያለውን ማሳወቅ የመሳሰሉ ስራዎችን በመከወን የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ያሟላል፡፡