📌ጎግል የአንድሮይድ ስልኮች የመሬት መንቀጥቀጥ መረጃ ጠቋሚ እንዲሆኑ አስችሎ ለገበያ አቀረበ
▫️የአልፋቤት ኩባንያ ምርት የሆኑት የጎግል አንድሮይድ ስልኮች በመላው ዓለም የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች አስቀድመው በመስጠት በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአደጋ እንዲርቁ አድርጎ በመሥራት ለገበያ አቅርቧል።
ይህንን ተከትሎ ካሊፎርኒያ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ማክሰኞ ዕለት የመጀመሪያዋ ግዛት ሆናለች።
ጃፓን፣ ሜክሲኮ እና ካሊፎርኒያ የመሬት መንቀጥቀጥ መረጃ በማግኘት ክስተቱ ከመፈጠሩ አስቀድሞ የሰዎችን ጉዳት እና የንብረት ውድመት ለመቀነስ እንዲቻል በመሬት ስር የተቀበሩ መረጃ ጠቋሚዎችን እንደሚጠቀሙ ኢቢሲ ሮይተርስን ጠቅሶ ዘግቧል።
ጎግል ያቀረበው የመሬት መንቀጥቀጥ መለየት እና ማንቃት ቴክኖሎጂ ውጤታማ ከሆነ፣ አደጋውን ለመቀነስ ዝቅተኛ ቴክኖሎጂ ያላቸው ኢንዶኔዥያ እና ሌሎች ታዳጊ አገራት ውስጥ ማስጠንቀቂያዎችን ለብዙ ሰዎች ማድረስ ያስችላል ተብሏል።
ጎግል ያማከራቸው የመሬት ውስጣዊ እንቅስቃሴ ባለሞያዎች ገና በሙከራ ሥራ ላይ ከሚገኝ ተግባር ከሚጠበቅ ቴክኖሎጂ ስሕተት እና የሕዝብ ደህንነት ወደ ግል ኩባንያ ከመግባቱ ስጋት በስተቀር ስማርት ስልኮችን አነስተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ መረጃ ሰጭ አድርጎ መሥራት ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል።
በዓለም ላይ ጥቂት ታብሌቶችን ጨምሮ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ስልኮች የጎግል አንድሮይድ መተግበሪያ እንዳላቸው ታውቋል።
ኩባንያው የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ወቅት የነበሩ ታሪካዊ የፍጥነት መለኪያ ንባቦችን በማጥናት አንዳንድ ተጠቃሚዎች እስከ አንድ ደቂቃ የሚደርስ መረጃ እንዲደርሳቸው ማድረግ እንደሚቻል እንደደረሰበት ተመልክቷል።
አሁን ደግሞ አንድሮይድ ስልኮች ኃይል በሚሞሉበት፣ በሚቀመጡበት እና የጎግል መረጃ ለማጋራት ፈቃድ በሚያገኙበት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥን ከመብረቅ አልያም ከሌሎች ምክንያቶች ከሚከሰቱ ንዝረቶች መለየት እንዲችሉ ማድረጉ ተገልጿል።
ስልኮች የመሬት መንቀጥቀጥ መረጃ ሲያገኙ ክስተቱ የሚፈጠርበትን ከተማ መገኛ ለጎግል በመላክ መነሻው እና መጠኑ ምን ያህል ነው የሚለውን ለማወቅ ያስችላልም ተብሏል።
ሆኖም ይህ ቴክኖሎጂ የጎግል ፕሌይ አገልግሎት ሶፍትዌሮች በታገዱባት ቻይና ውስጥ እንደማይሠራ ተገልጿል፡፡ @Tech_ethiopia_center