ቆይ ቆይ እስኪ እዚህ ጋር የቪኒስየስ ዡኒየር ጉዳይ ለግዜዉ ተከድኖ ይብሰል። ከዩሮ 2024 ፍፃሜ በፊት አለም ሁሉ እንደሚያዉቀዉ በሁለቱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ቪኒ ዡኒየር እና ጁድ ቤሊንግሀም መካከል ሁነኛ የባሎንዶር ፉክክር ሲደረግ እንደነበር አይተናል። ጉዳዩን የቀየረዉ አንድ ምሽት ብቻ ነዉ እሱም የዩሮ 2024 የፍፃሜ ጨዋታ ! በዛን ምሽት የሪያል ማድሪድ ደጋፊ ለሁለት ተከፍሏል ከአንድ ወገን ያሉት እንግሊዝ እንድትሸነፍ እና ዡኒየር ባሎንዶር እንዲበላ ይመኛሉ ፣ በሌላ ወገን ያሉት ማድሪዳዊያን ደግሞ እንግሊዝ ዋንጫዉን አሸንፋ ቤሊንግሀም በሪያል ማድሪድን በተቀላቀለ ገና በመጀመሪያ ሲዝኑ ባሎንዶር እንዲበላ ይመኛሉ።
አስታዉሱ በዚህ መሀል ማንም ሰዉ ሆነ ሚዲያ ሮድሪ ማን እንደሆነ እንኳን አያዉቅም። ከጨዋታዉ ፍፃሜ በኃላ እና ስፔን እንግሊዝን 2-1 ካሸነፈች በኃላ ግን በአንድ የ '90 ደቂቃ ምሽት ለዚህ ሽልማት አመቱን ሙሉ ሲፎካከሩ የነበሩት ሁለቱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ያልጠበቁት ነገር ተከሰተ "ሮዴሪጎ ሄርናዴዝ" ይቅርታ አድርጉልኝ እና ከጨዋታዉ በኃላ እንግሊዝ በመሸነፏ ደስ ካላቸዉ ማድሪዳዊያን መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ ፣ ለምን እንደማንኛዉም ደጋፊ የቪኒስየስ ዡኒየር ሁነኛ ተፎካካሪ ቤሊንግሀም እንደመሆኑ እና ሽልማቱ ከቪኒ የክለቡ የረጅም አመት ቆይታ አንፃር ይገባዋል ብዬ ስላሰብኩ ስፔን በማሸነፏ እጅግ በጣም ነበር ሀሴት ያደረኩት።
ነገር ግን ሮድሪጎ በአንድ ምሽት ብቻ የባሎንዶር አሸናፊ ይህናል የሚል ግምት እንደናተ ሁሉ እኔም አልነበረኝም። ሁኔታዉ በጣም አዝናኝ እና አስቂኝ ነዉ። የሁለቱን የ 2024 ስታስቲክስ ለግዜዉ ገታ ላድርገዉ እና ሁሉም Antimadridista ወይም የሪያል ማድሪድ ተቃዋሚዎች ሊቀበሉት እና ሊመልሱልኝ ያልቻሉት አንድ ከባድ ጥያቄ አለ። ምናልባት እዚህ የሪያል ማድሪድ ቤት ዉስጥ ያላችሁ ሪያል ማድሪድን የማትደግፉ ግን ከክለቡ የሚወጡ መረጃዎችን የምትከታተሉ ደጋፊዎች ካላችሁ ያዉ ትኖራላችሁም ይህን ጥያቄ መልሱልኝ። እምጠይቃችሁ እና እኔን ጨምሮ ብዙ ማድሪዲስታዎችን ሊያወዛግብ የቻለ ሁለተኛዉ Point ቢኖር Its not about junior ግን የሮድሪን ህይወት እደዚህ የቀየረዉ የ ዩሮ 2024 ዋንጫ ለምንድነዉ ለካርቫሀል ያልጠቀመዉ ?
በቁም ነገር ይሄ እኔ ላይ ብቻ ሳይሆን ሁላችሁም ላይ ጥያቄ ፈጥሯል ብዬ አስባለዉ። በባሎንዶር ሽልማት መስፈርት የዩሮ 2024 ዋንጫ ከቻምፒየንስ ሊግ ይበልጣል ተብሎ ቪኒ ዡኒየር ከተገገለ በኃላ ለምን ይሄን ሽልማት ላሊጋን ፣ ቻምፒየንስ ሊግን ፣ ሱፐር ካፕን እና ዩሮ 2024ትን ላሸነፈዉ ዳኒ ካርቫሀል አልተገባዉም ? ከሮድሪ አንፃር ካርቫሀል ብዙ ዋንጫ አሳክቷል why not this ? ብዙ መከራከሪያ ሀሳቦችን ልታመጡ ትችላላችሁ ፣ ከእነዚህም ዉስጥ አንዱ ሮድሪ ለስፔን የዋንጫ ስኬት ቁልፉ ሰዉ ነበር እንደምትሉኝም ጥርጥር የለኝም። ካርቫሀልስ ጎበዝ ? አረ አንዳንዴ ጭፍን ካለ ድፍን ካለ አስተሳሰብ ወጥተን ጉዳዩን እንመርምር እንዴ። 🤔 ሮድሪ ለስፔን ጎል አስቆጥሯል ብትሉኝ ደግሞ ካርቫሀልስ አላስቆጠረም ? ምንድነዉ ጉዱ ማመን ነዉ እንጂ ያቃታችሁ በሁሉም ነገር እኮ መንገዱ ተዘጋግቶባቹሀል። ሁሉም የሪያል ማድሪድ ደጋፊ የሆነ ወይም ያልሆነ "ምርጫዉ ተጭበርብሯል" የሚለዉ ዝም ብሎ አደለም በምክንያት ነዉ። እዉነታዉን ላለመቀበል ካልሆነ በስተቀር በቪኒ ዡኒየርም ሆነ በካርቫሀል ሁለት አሳማኝ Reason አቀረብን ከዚህ በላይ ምን እናድርግ። ብዙ ታላላቅ እርግ ኳስ ተጨዋቾች ዛሬ ማታ በቲዉተር ገፃቸዉ ወጥተዉ ሮድሪ ምርጥ አማካኝ እንደሆነ መስክረዋል። አዎ እኛም በዚህ ምንም ቅራኔ የለንም ነዉ። ነገር ግን ተጨዋቾቹ አስከትለዉ እንዳሉት ቪኒ ዡኒየር የዚህ ወቅት የአለማችን ምርጡ ተጨዋች ነዉ። አዎ ነዉ ይህ ሁሉም የሚያዉቀዉ ነዉ።
ብቻ ቢያንስ ለክርክር ስትገጥሙ አሳማኝ የሆነ ምክንያት ይዛችሁ ብትቀርቡ መልካም ነዉ እላለሁ። ካልሆነ ነገሩ ሰማኸኝ በለዉ ሰማኸኝ በለዉ ሆኖ ከመደነቋቆር ዉጪ ትርፉ ጉንጭ ማልፋት ነዉ።
HALA MADRID ALWAYS 🤍✌️
@ETHIO_REAL_MADRID_15