✅በፍቅሯ የወደቅኩት ገና ልጅ ሳለሁ ነበር። እቅጩን በቁጥር ለማስቀመጥ አልደፍርም።
✔️ ህልውናዬ ከሷ አይቀድምም። በፍቅሯ የነሆለልኩት በዚህ አመት ነው ማለት ከፍቅሬ የሚያጎድልብኝ ይመስለኛል። ሁሌም እንዳፈቀርኳት ነበር። ቀን ከወንበሬ ማታ ከመኝታዬ አትለየኝም። ይኸው ሀያ ምናምን አመት በፍቅሯ እንደተማረክሁ አለሁ።
ወሰን አልባ ፍቅር አለ ከተባለ የሁለታችን ነው። ቀኑን ሙሉ አብሬያት ውዬ ማታ እንደ አዲስ ትናፍቀኛለች። ፍፁም አልሰለቻትም። ለኔ ሁሌም አዲስ ናት። የማትጠገብ፣ የማትሰለች ናት። ሲፈጥራት እንዲሁ እፁብ ድንቅ አድርጎ ነው።
ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም። እሷ ግን አሮጌውን አለም በሙሉ አዲስ ገፅታ የማላበስ ሃይል አላት።
✔️ የተሰለቸውን የማደስ ጉልበት አላት። የኮሰመነውን የማግዘፍ፣ የደቀቀውን የማርቀቅ፣ የደከመውን የማጎልበት አቅም አላት። ለሷ ሁሉም ይቻላታል። በሷ መንደር የማይቻል የለም። ወሰን አልባ የምናብ ነፃነትን የማጣጥመው ከሷ ጋር ስሆን ነው። ከሷ ጋር እንደ እርግብ መብረር እንደ አሳ መዋኘት ይቻለኛል።
✅ ደግሞም ከሷ ጋር የምሆነው ደስ ሲለኝ አይደለም። ደስ የሚለኝ ከሷ ጋር ስሆን ነው። አብሬያት የምሆነው ከሌላ በተራረፈኝ ግዜዬ አይደለም። ዋናውን ግዜዬንም፣ ቀልቤንም፣ አትኩሮቴንም ለሷው ነው የምሰጠው።
እሷ ማናት? ካላችሁ
ውቧ ስነፅሁፍ ናት!!!
✅️⭐@Enmare1988
✅️✅️@Enmare1988