"ወሏሂ ዑራኤል ደግ ነው"
ተፃፈ @BiniGirmachew
ልክ ታቦታቱ ሲወጡ ነበር ዑራኤል የደረስኩት። ደመና ቢሆንም ምእመናን ከግቢው ተርፈው መንገዱን ዘግተውታል። በጭንቅንቁ መሀል ማለፍ እንደማልችል ሲገባኝ ካለሁበት ሆኜ ፀሎቴን አድርሼ ልመለስ ስል ግን ከኋላዬ ቆመው የሚለምኑት ሽማግሌ ቀልቤን ሰረቁት።
አይነ ስውር ናቸው፤ በዛላይ የሙስሊም ቆባቸውን ደፍተዋል፤ አንገታቸው ላይ ደሞ "ለአሏህ ብላችሁ ስለአይነብርሀን"የሚል ወረቀት አንጠልጥለው ከዘራቸውን እንደያዙ ቆመው ሳይ ባለማመን ለትንሽ ደቂቃ አስተዋልኳቸው የሚያልፈው ሁሉ ከቦርሳው እየፈተሸ ከኪሱ እየመዘዘ በሀዘኔታ የሽማግሌው ኪስ ውስጥ ብር እየጨመረ ሲያልፍ እሳቸውም ያለእረፍት እየመረቁ ስመለከት ደሞ ከምርቃታቸው ለመቀበል እኔም ተጠግቼ ያለቺኝን ኪሳቸው ጠብ አድርጌ ላልፈሰ ስል እጄን ይዘውኝ
አሏህ ይስጥልኝ...አሏህ ይጠብቅልኝ....ልጄ እባክህ መውጫው ጠፍቶኝ ይኸው ቆሜያለሁ ከዚህ ግርግር ውስጥ አስወጣኝ ልጄ..
እሺ አባባ ችግር የለውም... ግን እንዴት እዚህ ግርግር ውስጥ(የምለው ጠፍቶኝ ዝም አልኩ አይ የዛሬውስ ተአምር ነው።እኔ እዚህ እመጣለሁ ብዬ መች አሰብኩና።
ባለቤቴ ታማብኝ አልጋ ከያዘች ቆየች የሚረዳን የለም። እሷን ማሳከም አደለም ማጉረስ አቅቶኝ ጠዋት ዱአ አድርጌ ለልመና ስወጣ ከአንድ እንደኔው ካረጁ ሽማግሌ ጋ ተገናኘን።መንገድ ሊያሻግሩኝ ሲሉ ብቻ ችግሬን ነገርኳቸው። እሳቸውም ከኔጋ ብትመጣ ብዙ ብር ታገኛለክ አሉኝ።እኔም አምኜ ተከትያቸው እዚህ መጥተን ግርግሩ መሀል ስንደርስ ግን መጣሁ ብለውኝ ተሰወሩ።
ስማቸውን አላቅም።
ነጠላ መልበሳቸውን ብቻ አስታውሳለሁ በመሀል በመሀል ደሞ አይዞህ ኡራኤል ደግ ነው ይሉኝ ነበር።ታድያ እኔ እስኪመጡ ብዬ በቆምኩባት ቅፅበት ሰወች እየመጡ ብር በኪሴ ይከቱልኝ ጀመር።ይሄኔ ደነገጥኩኝ ሰውየው ለምን እዚህ እንዳመጡኝም ገባኝ።
አፌን አውጥቼ አለመንኩም፤ ቤተክርስትያን ጋ መሆኑን አውቄም ስለ አሏህ አላልኩም፤እጄንም አልዘረጋሁም!!የሚሆነው ነገር ቢደንቀኝ ግን የሚሰጡኝን ተቀብዬ በማውቀው አሏህ ይስጥልኝ እያልኩ እየመረቅኩ ኪሴ ሲሞላ አንተ ደረስክ።
ይኸው ብር በብር ሆንኩኝ የለመንኩት አላሳፈረኝም ሰውየውም ደግ ብለው የጠሩት ኡራኤል ቸል አላላቸውም።የኔ ልጅ ምንም ችግር ቢገጥምህ ፈጣሪህ ጥሎ አይጥልህምና እምነትህ በሱ ይሁን። አንተም ደሞ ሁሌ ለሰወች ደግ ሁን "በሚታየው እጅህ ስትሰጥ የማይታየው የአምላክ እጅ ይከተልካል' እኔ ቤተክርስትያን
ደጅ ደርሼ አላቅም።
ዛሬ ግን ብመጣ ከምግብ አልፎ ሚስቴን የማሳክምበት ብዙ ብር ኪሴን ሞላው።አየህ ክርስትያኑ ሙስሊም ነው ብሎ በንፍገት አላለፈኝም ደግነት ዘር የለውም፤ሀይማኖት የለውም ፤ቋንቋ የለውም ፤ማንም ማንንም ቢረዳ አምላክ ለሱ ጨምሮ ይሰጠዋል እንጂ የዋጋውን አያጣም።
አሁን ደስ ብሎኛል ሚስቴም ትታከማለች ጭንቄ ቀሏል የሠጠኝ አይጉደልበት አሏህ ይጨምርላችሁ ደሞ ሚስጥር ልንገርህ??(እጄን ጠበቅ አድርገው ጆሮዬ ስር እየተጠጉ እሺ አባባ ይንገሩኝ ምንድነው? ) አልኳቸው የሚሉኝን ለመስማት እየጓጓሁ
"ወሏሂ ኡራኤል ደግ ነው"ብለውኝ የእውነት ሳቁ እኔም የእውነት ደስ ብሎኝ እየሳቅኩ ታክሲ አስይዣቸው መርቀውኝ ተለያየን።
"ወሏሂ ኡራኤል ደግ ነው"
@Eotc_Books_By_Pdf