ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ ትችላለች⁉️
➦በወር አበባ ጊዜ የሚከለከልስ ጸሎት አለ?
➦ተወዳጆች ሆይ ሴት ልጅ በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታያት ከሱባኤ የመውጣትና የመቆየቷ ነገር እንደ ገዳሙ ሥርዓት ይወሰናል፡፡ ከሱባኤ ትወጣለች ማለት ሱባኤን (አርምሞን) ትፈታለች፣ተአቅቦዋን ትተዋለች ማለት ሳይሆን እስከምትነፃ ድረስ ገዳሙ ባዘጋጀው ቦታ ቆይታ መጨረስ ትችላለች፡፡ በሱባኤው ላይ ወይንም መውጫው ሲቃረብ የወር አበባ ቢታያት ሱባኤውን ማቋረጥ ሳይሆን በጊዜያዊ ቦታ መጨረስ ይገባታል፡፡
ብዙዎች እህቶቻችን ሱባኤ የምንይዙት በድንገት ነው፡፡
➦ይህ ችግር እንዳይገጥማችሁ ሱባኤ ከመግባታችሁ በፊት ቀናችሁን ቆጥራችሁ አስተካክላችሁ ብትይዙ የበለጠ ትጠቀማላችሁ፡፡ ሰይጣን ያለጊዜው በወር አበባ ሊፈትናችሁ ስለሚችል ቀናችሁን እንደጨረሳችሁ ሱባኤ ብትይዙ ይመረጣል፡፡ በተለይ ዓይነ ጥላ ከዓይነ ጥላም ገርግር ዓይነ ጥላ ያለባቸውና መተት እና ድግምት የተደገመባቸው እህቶቻችን ያለ ጊዜና ያለ ቀኑ በሚመጣ የወር አበባ በሱባኤ ወቅት ይፈተናሉ፡፡ ምስጋና ለእመቤታችን ይሁንና እመቤታችን ንፁህ አይደላችሁም በማለት ጸሎታችሁን ቸል ስለመትል የያዛችሁትን ሱባኤ ቀጥሉ፡፡ ምክንያቱም የእኛ ርኩሰት የእመቤታችንን ንፅህና ስለማያሳድፍ ጸሎታችንን ትሰማናለች፡፡
➦ጸሎት ከፈጣሪ የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ እግዚአብሔር ጊዜን እየጠበቀ በዚህ ጊዜ እሰማችኋለሁ በዚህን ጊዜ አልሰማችሁም አይልም፡፡ በወር አበባ ጊዜ አይጸልይም ማለት የቤተ-ክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን የሰነፉ ሰይጣን የተንኮል እና የእንቅፋት ስብከት ነው፡፡ የሰይጣንን እንኳን ጸሎት ትተን ቀርቶ እየጸለይን ፈተናችንን እኛና እግዚአብሔር ነው የምናውቀው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ እንደ እኛ ግራ ለተጋቡት የተሰሎንቄ ምእመናን "ሳታቋርጡ ፀልዩ" በማለት ፀሎት በየትኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ፅፎላቸዋል።
➦ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እስከ መንጻቷ ቤተ-ክርስትያን ነው መግባት የማትችለው እንጂ፣ ጸሎት ማቋረጥ የለባትም፡፡ ጊዜን ተብቆ አለመጸለይ ለሰይጣን በር መክፈት ነውና ትንሿን ጸሎታችንን ማቋረጥ የለብንም፡፡
ተወዳጆች ሆይ ጌታችን ደመኛን እንጂ ደምን አይጠየፍም አይጠላም፡፡ ቢጠየፍማ ለአሥራ ሁለት ዓመት ሰውነቷ በደም ሲጨቀይባት የነበረችውን ምስኪን ሴት መለኮት ጋ ጠጋ ብላ ልብሱን ነክታ ልትድን ቀርቶ መርገምንና ሌላ በሽታን ሸምታ በተቀሰፈች ነበር፡፡ ጌታችን ግን መልካም አመጣጧን ፣ የዓመታት ጭንቀቷን ተመልክቶ ከነደሟ ተቀብሎ በልቧ የነበረውን አውቆ ፣ የደሟን ምንጭ አድርቆ፣ እምነቷን አድንቆ፣ ከጤናዋ ጋር በሰላም ወደ ቤቷ መልሷታል፡፡ /ማቴ. 9፣18-26, ማር. 5፣21-43, ሉቃ. 8፤41 ይመልከቱ/
ወለላይቱ የእመብርሃን ልጆች የእመቤታችንን ባህርይ አላወቅንም እንጂ፤ እርሷ ጥዩፍነት ከቶ በባህሪዋ የለም፡፡
➦የዛሬውን አያድርገውና ሁላችንም ስንወለድ እናቶቻችን በምጥ ሰዓት ከነደማቸው በጸሎትና በጭንቀት ጠርተዋት አወዋልዳቸዋለች፤ አሁንም ታዋልዳቸዋለች፡፡ በአራስራቸው ጊዜ ከእነሱ አትለይም፣ እስከ ስሙም ‹የማርያም አራስ› ተብለው በስም ይጠራሉ፡፡
ሌሎች በወር አበባ ጊዜ አይጾምም ይላሉ፣ ከየት እንዳገኙት ባይገባኝም ይህች በወር አበባ አመካኝቶ፣ለመብላት አንኩቶ ይመስለኛል፡፡ በወር አበባ ጊዜ አንዳንድ እህቶቻችን ከፍተኛ የሕመምና የስቃይ ስሜት የሚሰማቸው ብሎም እስከ ሕክምና የሚያደርሳቸው ከሆነ ምናልባት መድሃኒት ሊወስዱ ስለሚችሉ እነርሱን አይመለከትም፡፡
➦ስለዚህ ያስለመድናቸውን ጸሎቶች ሁሉ መጸለይ እንችላለን፡፡ እራሳችሁን ከኃጢአት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ አንደበታችሁን ከሐሜት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ ሥራችሁን ከወር አበባ አንጽታችሁ፣በልባችሁ ማህደር ቂም እና ክፋት ቋጥራችሁ ብትጸልዩ ምን ዋጋ አለው? ከአንድ ሳምንት ከመርገም ጨርቅ ይልቅ በኃጢአት፣በክፋት ከሚጨማለቅ ሰውነት የሚቀርብ ጸሎት ከደመና በታች ነው፡፡ የወር አበባ በአንድ ሳምንት ይነጻል፡፡
ግን ከሰውነታችን አልነጻ ያሉን ስንት ኃጢአቶች አሉ፡፡
ስለዚህ ንጹህም ሆንን አልሆንን በርትተን ተግተን
ልንጸልይ ይገባል፡፡
👉🏽 ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን⁉️
የሚለውን እንመለከታለን።
🙏እስከዛው ይሄንን ለወዳጅዎ ለጓደኞችዎ ለሴት እኅቶች ያጋሩት🙏
ይቀጥላል...
•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺