⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Books


በዚህ ቻናል የሚቀርቡ
፩.ተከታታይ የቤተክርስቲያን ትምህርቶች ፣
፪. መንፈሳዊ መጻሕፍት ጥቆማ፤
፫. የተለያዩ አጫጭር የቤተክርስቲያን መጣጥፎች ፣ ወጎች ፣ ታሪኮች ፤
፬. ለተለያዩ ጥያቄዎች መልስ እና ወቅታዊ ትምህርቶችን እንማማራለን ፣
፭. ዘወትር #ቃለ_ወንጌል የእለቱ(በግፃዌ) ይቀርባሉ።
ተከታታይ ትምህርቶች ለማግኘት 👇👇
@EOTC_teketatay
ለጥያቄ👉 @Temechache

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Books
Statistics
Posts filter


ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።

በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።

እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ


#ቃለ_ወንጌል

ዘሰንበተ ክርስቲያን
        ሉቃስ 9:18-28


   ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት፤ እርሱም ለብቻቸው ይዞአቸው ቤተ ሳይዳ ከምትባል ከተማ አጠገብ ወደ አለ ምድረ በዳ ወጡ። “ሕዝቡም ዐውቀው ተከተሉት፤ እርሱም ተቀበላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም አስተማራቸው፤ ሊፈወሱ የሚሹትንም አዳናቸው።

ቀነም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፥ “ያለንበት ምድረ በዳ ነውና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩ የሚበሉትንም እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት” አሉት። "እርሱ ግን፣ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው” አላቸው፥ እነርሱም፡ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ልንገዛ ካልሄድን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለንም” አሉት።

"ሰዎቹም አምስት ሺህ ያህሉ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱንም፥ “አምሳ አምሳውን በየክፍላቸው አስቀምጡአቸው” አላቸው። “እንዲሁም አደረጉ፤ ሁሉም ተቀመጡ። "አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመለከተ፤ ባረከ፤ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው: ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ያነሡትም የተረፈው ቍርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ::


#መልእክታት
1ቆሮንጦስ 2:1-12
1ጴጥሮስ 2:20-ፍጻሜ
ሐዋ፡ሥራ 4:19-31

ምስባክ
    መዝ· ፷፯ ቍ· ፳፰ – ፳፱

ወአጽንዖ እግዚኦ ለዝንቱ ዘሠራዕከ ለነ

ውስተ ጽርሕከ ዘኢየሩሳሌም

ለከ ያመጽኡ ነገሥት አምኃ

ትርጉም

አቤቱ፥ ይህንም ለእኛ የሠራኸውን አጽናው።

በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ፡

ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ።


"ብርሃን ወደ አንድ ቤት ውስጥ ሲገባ ጨለማን እንደሚያስወግድ ሁሉ፤ እግዚአብሔርን መፍራት ወደ አንድ ሰው ልብ ሲገባም አለማወቅን (በኃጢአት የሚወድቅባትን) ያስወግዳል።"

አባ እንጦንስ


#ቃለ_ወንጌል

23/01/2019
         ማርቆስ 13:11-32

       ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፥ በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፥ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ። በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤ በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና።

ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ። በዚያን ጊዜም ማንም እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ። እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ። በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል። ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም::

#መልእክታት
2ጢሞቴዎስ 2:1-14
1 ጴጥሮስ 1:6-10
ሐዋ፡ሥራ 24:11-22

                                     
ምስባክ

          መዝሙር ፶፱ : ፫ – ፬

ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ

ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት

ወይድኀኑ ፍቁራኒከ

ትርጉም

ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው

ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ

ወዳጆችህም እንዲድኑ


Forward from: ግእዝ ለኵሉ
ግበሩ ፈንዎ .. ሼር ይደረግ


ጥያቄ:- እንዴት የተለያየ ዓይነት ዜማ ብሂል ሊኖር ቻለ? የትኛው ነው ትክክል?

መልስ፦ በየሀገሩ ሥርዓተ አምልኮን ለመፈጸም ልዩ ልዩ የዜማ ስልቶች አሉ። የአርመን ቤተክርስቲያን፣ የግብጽ ቤተክርስቲያን፣ የሶርያ ቤተክርስቲያን፣ የሕንድ ቤተክርስቲያንና የሌሎችም የየራሳቸው ዜማ አላቸው። ዜማው እግዚአብሔርን ማመስገኛ እስከሆነ ድረስ መለያየቱ የሚፈጥረው ችግር የለም። በሀገራችንም የአጫብር ዜማ፣ የቤተልሔም ዜማ፣ የቆሜ ዜማ፣ ወንጨሬ፣ ተጕለቴ...ወዘተ እየተባለ ልዩ ልዩ ዜማዎች አሉ። በሁሉም የሚመሰገን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ጉዳዩ በንጽሕና ማገልገሉ ላይ እንጂ የዜማው ልዩነት የሚፈጥረው ችግር የለም። ሁሉም እግዚአብሔር እስከተመሰገነበት ድረስ ትክክል ነው።

ጥያቄ:- በነገረ ሥጋዌ ርስት መቼ ይነገራል?

መልስ፦ ርስት የሚለው ቃል ወረሰ ከሚለው ግሥ የወጣ ምዕላድ ነው። በነገረ ሥጋዌ ምስጢሩ ሥጋ የቃልን ገንዘብ ቃልም የሥጋን ገንዘብ መውረሳቸውን የሚያመለክት ቃል ነው። በጊዜ ተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ ስለሆነ ርስት ከጊዜ ተዋሕዶ ጀምሮ ይነገራል።

በትረ ማርያም አበባው


Forward from: Henok Haile
+ መርጦ መወለድ +

ከእገሌ ልወለድ ብሎ መርጦ የተወለደ የለም:: ምረጡ ብንባል ምን ዓይነት ወላጅ እንመርጣለን? ቀድመን የመገምገም ዕድል ቢኖረን ምን ዓይነት ወላጆች እንመርጣለን። መቼም በወላጆቼ ደስተኛ ነኝ የሚል ሰው "እኔ ደግሜም ብወለድ ከአባዬ ከእማዬ ነው መወለድ የምፈልገው" ማለቱ አይቀርም። ግን ደግሞ ዕድሉን ቢያገኝ መቼም ትንሽም ቢሆን የሚያስተካክለው ነገር አይጠፋም። መርጦ መወለድ አይቻልም እንጂ ቢቻል የምንመርጠው ልዩ ምርጫ ይሆናል።

መርጦ የተወለደ ክርስቶስ ብቻ ነው። በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ተመልክቶ መዓዛዋን መርጦ ፣ በቅድስናዋ ውበት ተማርኮ ከእርስዋ ሊወለድ የመረጣት የተመረጠች እናት ድንግል ማርያም ብቻ ናት። የፈጣሪ ምርጫ እንደ ሰው አይደለም። ሰው ፊትን ያያል እርሱ ግን እስከ ልብ ድረስ ዘልቆ ይመለከታል። እንዴት ብትነጻ ፣ እንዴት ብትቀደስ ነው? እስከ ውስጥዋ ዘልቆ አይቶ ከእርስዋ ሊወለድ የመረጣት? ንጉሥ ውበትዋን የወደደላት ፣ ለእናትነት የመረጣት ቅድስት እንዴት የከበረች ናት?
አዎ መርጦ የተወለደ የለም ፣ ክርስቶስ ግን መርጦ ብቻ ሳይሆን ፈጥሮ የተወለደ ነው። መቅደሱን አንጾ የገባባት እርሱ ነው። መርጦ ለተወለደብሽ ለአንቺ በጸጒራችን ቁጥር ምስጋና እናቀርባለን።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


Forward from: Crypto
$ATF Airdrop

◦ 1 ሰው ስትጋብዙ 100 ATF ($0.19 ) ስለሚሰጣችሁ 500 ATF ስትደርሱ ማውጣት ትችላላችሁ ብዙ Account ያላችሁ እድሉ እንዳያምልጣችሁ ተጠቀሙበት  ።

➯ በዚህ Link ግቡ  : https://t.me/ATF_AIRDROP_bot?start=901374580

➯ Start ብላችሁ ከ Ton wallet ጋር Connect አድርጉ
➯ Mining አስጀምሩ
➯ ሁሉንም Social Task ስሩ
➯ ጀለሶቻችሁን invite አድርጉ
➯ Done ✌️

◦ ሰው ጋብዛችሁ አልቆጥር ካላችሁ invite ያደረጋችኋቸውን ሰዎች ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ወደ አካውንታቸው ተመልሰው ገብተው mine ያደረጉትን claim እንዲያደርጉ ንገሯቸው ያኔ invite commission(100 $ATF) ይገባላችኋል 👌


ውድ ወንድሜ ሰውን በስብከት ማገልገል የግድ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይደለም፣ ትልቁና ዋነኛው ሰውን በራስ ሕይወት መለወጥ ነው፡፡ ስለዚህ በሕይወትህ ለብዙዎች አብነት እንድትሆን እንጂ የግድ ስብከት አዘጋጅተህ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይጠበቅብህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰው ከሆንክ ሰዎች ፊትህን ባዩት ጊዜ የዋህነትን፣ ሩህሩህነትን ይማራሉ፣ ንግግርህንም በሰሙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራነት፣ ታማኝነት፣ ፍፁምነትና ፍቅርን ያገኛሉ፡፡
ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ


#ቃለ_ወንጌል

22/01/2019
       ማርቆስ 13:9-14

     እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።
ሲጎትቷችሁና አሳልፈው ሲሰጧችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሏቸውማል በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል::
#መልእክታት
2 ቆሮንጦስ 4:7-ፍጻሜ
1 ጴጥሮስ 4:12-ፍጻሜ
ሐዋ፡ሥራ 19:8-11
ምስባክ
         መዝሙር 33:19-20
ብዙኅ ሕማሞሙ ለጻድቃን
ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር የዐቅብ ኵሎ አዕፅምቲሆሙ
ትርጉም
የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥
እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል።
እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥


"ጌታ ሆይ ወርቅ ትሰጠኝ ዘንድ አልለምንህም፤ ሀብት ንብረትም አልለምንህም፤ እነርሱ ድኅነትን የሚያስገኙ አይደሉምና። ይቅርታህን ማግኘት ግን ከወርቅ ይልቃል። የኃጢአት ሥርየትን ማግኘትም ከብር ይበልጣል።"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ


ጥያቄ:- በጳጕሜን ሳምንት ብዙዎች ሰዎች የጳጕሜን ውሃ ጠበል ነው እያሉ ወንዝ ወርደው ይታጠባሉና ይህ እንዴት ነው?

መልስ፦ ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ ድፍርስ የነበረው ውሃ ይጠራል። ስለዚህ ሰው በምክንያት ወንዝ እየሔደ ይታጠባል። እንጂ የወንዙ ውሃ ጠበል ይሆናል ማለት አይደለም። በጳጕሜን ወንዝ እየሄዱ መጠመቅ ኢዮብ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ቀን ተጠምቆ የመዳኑ ምሳሌ ነው። ስለዚህ ጠበል ካለ ከጠበል ቦታ እየሔዱ መጠመቅ ነው። ጠበል ከሌለ ደግሞ የኢዮብን መጠመቅ እያሰብን ወደማንኛውም ወንዝ እየወረድን መታጠብ ነው።

ጥያቄ:- ዲቁና ተቀብያለሁ እና ሳላገለግል ከሸፈብኝ። አሁን እኔ ቅኔና መጽሐፍ መማር እችላለሁ?

መልስ፦ ትችላለህ። ቅኔን፣ መጽሐፍን ሴቶችም ይማሩታል። ሴቶች ክህነት ኖሯቸው አይደለም። የመጽሐፍ ትምህርት ሃይማኖትን ለማወቅ፣ ሥነ ምግባር እንዲኖረን ለማድረግና ለመሳሰለው ትልቅ ጥቅም ስላለው ማንኛውም ክርስቲያን መማርና ማወቅ ያለበት ትምህርት ነው። ክህነትህ ከፈረሰ በክህነትህ አትቀጥልም። ከመማር ግን አትከለከልም።

ጥያቄ:- እዚህ ምድር ላይ ያለ ሁሉም ሳይወድ እና ሳይፈቅድ ነው ወደዚህ ምድር የመጣው። እና ያለ ፈቃዱ በመጣባት ምድር በሚኖረው ሕይወት በሠራው ሥራ ወደ ሲኦል መውረዱ ከእግዚአብሔር ፍትሐዊነት ጋር አይጋጭም?

መልስ፦ አይጋጭም። አዎ የሰው ልጅ ለመፈጠሩ ምክንያቱ የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ነው። ሰው ቀድሞ ስላልነበረ ሲፈጠር አስተያየት መስጠት አይችልም ነበር። ነገር ግን ከተፈጠረ በኋላ ከሲኦልና ከገነት የፈለገውን መርጦ የመኖር ሥልጣን ተሰጥቶታል። ስለዚህ ሲኦልም የሚገባ ገነትም የሚገባ በዋናነት በራሱ ምርጫ ነው። ከእግዚአብሔር ፍትሓዊነት ጋር ምንም የሚያጋጨው ነገር የለም። እንዲያውም ይህ የሚያሳውቀን የሰውን ምርጫ የሚያከብር እግዚአብሔር ምን ያህል ፍትሓዊ እንደሆነ ነው። ሰው ያለፈቃዱ ወደዚህ ዓለም መጣ እንጂ ወደ ሲኦል ያለፈቃዱ አልገባም። ጠያቂ ሆይ ቀላቀልከው። ሰው ሲኦል የሚገባ በራሱ ምርጫ ነው። የምርጫው መገለጫ ደግሞ ክፉ እየሠራ በመኖሩ ይታወቃል። የሰው ልጅ ምን ቢሠራ ገነት፣ ምን ቢሠራ ደግሞ ሲኦል እንደሚገባ ተገልጿል። ስለዚህ የሚመቸውን መርጦ መሥራት የራሱ የሰው ድርሻ ነው።


#መስከረም_21

#ብዙኃን_ማርያም

በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም 21 ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤

#ጉባዔ_ኒቅያ
በ325 ዓ.ም አርዮስ የሚባል መ*ና**ፍ*ቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአር*ዮስ ክህ*ደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሠረት ከሚያዝያ 21 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ 2348 ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡

ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር 9 ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ2348ቱ መካከል 318 ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ 318ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት 318ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው (ዘፍ.14፥14)፡፡

318ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር 9 ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም 21 ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡

#ዕፀ_መስቀል
በሌላ በኩል መስከረም 21 ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤

ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡

ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡

መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ1446 ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም 21 ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡

(#ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረገጽ)


#ቃለ_ወንጌል

21/01/2019
            ሉቃስ 1:39-57


     ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት። ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።  ማርያምም እንዲህ አለች ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።

ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል። በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።  ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች::


#መልእክታት
1 ቆሮንጦስ 5:3-ፍጻሜ
2 ዮሐንስ 1:4-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 19:17-21
                  
ምስባክ


             መዝ 44:9

ወትቀውም ንግስት በየማንከ

በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኅብርት

ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ

ትርጉም

ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች

በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ተሸፋፍና

ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ


Forward from: ያሬዳውያን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማኅሌት ዘመስከረም ብዙኃን ማርያም
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ስቡህ ከተባለ በኃላ
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ንባርኮ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ንፍሑ ቀርነ በጽዮን፤ ስብኩ በዓለ ማርያም ወበዓለ መስቀል ዘዮም።
@EOTCmahlet
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዓይ ይእቲ ዛቲ መድኃኒት እንተ ኃሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኅ ግበር ታቦተ በዘትድኅን እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ።

መልክአ ማርይም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ፍጽመነ ንዕትብ በዕፀ መስቀሉ፤ ነግሀ ነቂሐነ እምንዋም በከመ ይቤሉ አዕማደ ሰላም፤ ዘዮም መስቀል አሠነየ ዓለመ እንተ በልየ፤ በስነ ማርያም አዋከየ፤ ለክርስቲያን ኮኖሙ ዕበየ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ዮም መስቀል አሠነየ እንተ በልየ ዓለመ አሠነየ/፪/
በስነ ማርያም አዋከየ በስነ ማርያም/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ ዘግምጃ ቤት
ወይቤልዋ እምነ ጽዮን በሐ ወይቤልዋ ደብተራ ፍጽምት በሐ ወይቤልዋ ብርሃነ አህዛብ በሐ ወሪዶ እመስቀሉ ሙቁሐነ ፈትሐ

መልክአ ማርያም
ሰላም ለጒርዔኪ ሠናይ እምወይን፤ በከመ ይቤ ሰሎሞን፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ብርሃን፤ ክድንኒ ገርዜነ ጸጋ ኢያዕጽበኒ ዕርቃን፤ ዘኢአነምዎ ጠቢባን በኪን።
@EOTCmahlet
ዚቅ
በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም፤ ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ጽጌ ደመና፤ መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም፤ ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን፤ ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን፤ አጽገዩ ሕዝበ ወመሐይምናን፤ በቤተ መርዓ ተመልዑ ክርስቲያን።
@EOTCmahlet
ወረብ
ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን/፪/
ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ማርያም፦
ሰላም ለሐቌኪ በትረ ሌዋዊ ሣውዕ፤ዘኢሐፀነኪ ጠል ወዘኢሰቀየኪ ነቅዕ፤ማርያም ድንግል እግዝእተ መላዕክት ወሰብዕ፤ሰድኒ ብሔረ ፍግዕ በትንባሌኪ ባቍዕ፤ምስለ ኅሩያንኪ ደርገ አሀሉ በስንዕ።

ዚቅ፦
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አሕዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ

መልክአ ማርያም
ሰላም ለመልክዕኪ ዘተሠርገወ አሚረ፤ ዘያበርሕ ወትረ፤ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ፤ አርእይኒ ገፀ ዚአኪ ማርያም ምዕረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ
@EOTCmahlet
ዚቅ
አብርሂ አብርሂ ማርያም አብርሂ፤ መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትትሞጥሒ፤ ጽዮን ዮም ተፍሥሒ።
@EOTCmahlet
ወረብ
አብርሂ አብርሂ ማርያም አብርሂ አብርሂ/፪/
መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትትሞጥሒ ጽዮን ዮም ተፈሥሒ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ ዘግምጃ ቤት-
ፍጽመነ ንዕትብ...

መልክዐ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ: ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ: ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ: ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ: ዘጸገየ ማሕጸንኪ አፈወ ነባቤ።

ዚቅ
ሐፁር የዓውዳ ወጽጌረዳ ግብተ በርሃ ገጻ እምጸሐይ በትእምርተ መስቀል ክቡራት ዕንቊ መሠረታ

ወረብ፦
ግብተ በርሃ ገጻ እምጸሐይ በርሐ ገጻ ግብተ እምፀሐይ/፪/
ክቡራት ዕንቍ መሠረታ ሐፁር የዓውዳ ወጽጌ ረዳ በትምህርተ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
ማህሌተ ጽጌ
ብሩካን አርጋብ...
ዚቅ፦
ወበእንተዝ አዘዙነ መምህራነ ቅዱስ ወንጌል፤ አምሳለ ፈጣሪ ልዑል፤ ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ድንግል።

ወረብ፦
ወበእንተዝ አዘዙነ መምህራነ ቅዱስ ወንጌል ወንጌል አምሳለ ፈጣሪ ልዑል /፪/
ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ድንግል  ማርያም ድንግል/፪/
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
ዓይ ይእቲ ዛቲ መድኃኒት፤ እንተ ኃሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት፤ ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኅ፤ ግበር ታቦተ በዘትድኅን፤ እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ፤ አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ።
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
አክሊለ ተቀጺላ/፪/
አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ/፬/
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል፤ ይእቲኬ ቤተ ምስአል፤ ዘአስተዓጸቡ ታቀልል፤ ለኲሉ ፍጥረት ትተነብል፤ በአክናፈ መላእክት ትትኬለል፤ ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፤ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፤ መንክር ወመድምም ዕበያ ወክብራ ለድንግል፤ ጽሕፍት ውስተ ወንጌል፤ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።
@EOTCmahlet
አመላለስ
ጽሕፍት ውስተ ወንጌል/፪/
ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
ዓዲ እስመ ለዓለም
ጸሎትክሙ ጽንዕት ሃይማኖትክሙ ርትዕት፤እንተ በኵሉ ትረድዕ፤ሠናያን ወውርዝዋን በምግባረ ጽድቅ አግዓዝያነ አንትሙ፤እለ መነንክምዎ ለዝንቱ ዓለም ኃላፊ፤ከመ ነግድ ፈላሲ ሀልዉ አኃውየ ፍቁራንየ፤ምንት ይበቁዓነ ንብረቱ ለዝንቱ ዓለም፤ኢትርሲቶ ለዝንቱ ዓለም፤ኢወርቅ ሤጡ ለነፍስክሙ፤ሀቡ ናጥብዕ ወንንሣእ መስቀለ ሞቱ ለፍጹም መድኃኒነ፤ኢየሱስሃ ክርስቶስሃ ሰብሕዎ፤ሀቡ አኰቴተ ለስብሐቲሁ፤እንዘ አልብነ ኵሉ ብነ፤እንዘ አልቦ ዘየአምረነ ብዙኃነ የአምሩነ፤ንልበስ ልብሰነ ዘድልው ለነ በኃቤሁ፤ማኅደርነ ዘበሰማያት።

🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    # Join & share #


ጥያቄ:- ካህን እና ዲያቆን ዐሥራት በኵራት ይከፍላሉ ወይስ አይከፍሉም?

መልስ፦ ይከፍላሉ። በብሉይ ኪዳንም ሌዋውያን ዐሥራት ያወጡ ነበር። ካህናት የሚኖሩት በዐሥራት በኵራት ገንዘብ ነው። ስለዚህ በዐሥራት በኵራት ካገኙት ገንዘብ ዐሥራትን ስለሚያወጡ የእነርሱ አሥራት የዐሥራት ዐሥራት ይባላል። "ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን ዐሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የዐሥራት ዐሥራት ታቀርባላችሁ" እንዲል (ዘኍ.18፥26)።

ጥያቄ:- አብላካት እና አብሳላት ብሎ ስም ማውጣት ይቻላል ወይ?

መልስ፦ ይቻላል። ሁላችንንምኮ በተፈጥሮ ወደዚህ ምድር ያመጣን አብ ነው። ስለዚህ አንዲትን ሴት እግዚአብሔር እንደፈጠራትና ወደዚህ ዓለም እንዳመጣት ለመመስከር አብላካት አብሳላት ብትባል የሚያመጣው የምስጢር መፋለስ የለም።

ጥያቄ:- ጳጕሜን 3 ሰማይ ይከፈታል ይባላል። አከፋፈቱ እንዴት ነው? የሚከፈትበት ምክንያትስ ምንድን ነው?

መልስ፦ ሰማይ የሚከፈት የሚዘጋ ነገር አይደለም። ብዙ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስም የምስጢር መገለጥን፣ የምሕረት መውረድን የሰማይ መከፈት እያለ ይገልጸዋል። ጳጕሜን 3 ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል መታሰቢያ በዓሉ ነው። በዚህ መታሰቢያ በዓሉ በምልጃው ብዙዎችን ይጠቅማልና ይህንን ለመግለጽ ሰማይ ይከፈታል እየተባለ ይነገራል እንጂ ይህ ወደላይ የምናየው ሰማይስ አይከፍትም አይዘጋም።

ጥያቄ:- አንድ ዲያቆን ቅዳሴ ከገባ በኋላ ነስር ቢነስረው አቋርጦ መውጣት ነው ያለበት ወይስ እስከ መጫረሻው ቆይቶ መቁርብ ነው ያለበት?

መልስ፦ አቋርጦ መውጣት ነው ያለበት። አንድ ሰው አካሉ ከደማ በቤተክርስቲያን እንዳይፈስ በልብስ አፍኖ ወዲያውኑ መውጣት አለበት። ቅዳሴውን በቀሩት ልዑካን መፈጸም ነው።

© መምህር በትረ ማርያም አበባው


"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


#ቃለ_ወንጌል
20/01/2019
         ዮሐንስ 10:1-22

    እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማይገባ፥ በሌላም በኩል የሚገባ ሌባ፥ ወንበዴም ነው። በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው። "ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ቃሉን ይሰሙታል፤ እርሱም በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል። ሁሉንም አውጥቶ ባሰማራቸው ጊዜ በፊት በፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ይከተሉታል፤ ቃሉን ያውቃሉና። ሌላውን ግን ይሸሹታል እንጂ አይከተሉትም፤ የሌላውን ቃሉን አያውቁምና።” ጌታችን ኢየሱስም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገ ራቸውን አላወቁም።

ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ነገር ግን፤ በጎች አልሰሙአቸውም። እውነተኛዉ የበጎች፤ በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩልም የሚገባ ይድናል፤ ይገባልም ይወጣልም፤ መሰማርያም ያገኛል። ሌባ ግን ሊሰርቅና ሊያርድ፥ ሊያጠፋም ካልሆነ በቀር አይመጣም፤ እኔ ግን የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኙ፥ እጅግም እንዲበዛላቸው መጣሁ።

“ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል። "ጠባቂ ያይደለ፥ በጎቹም ገንዘቡ ያይደሉ ምንደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም መጥቶ በጎቹን ይነጥቃቸዋል፥ ይበትናቸዋልም። "ምንደኛስ ይሸሻል፤ ስለ በጎቹም አያዝንም፤ ምንደኛ ነውና። ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን መንጋዎቼን አውቃለሁ፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል። አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን አውቀዋለሁ፤ ለበጎችም ቤዛ አድርጌ ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ። ከዚህ ቦታ ያይደሉ ሌሎች በጎችም አሉኝ፤ እነርሱንም ወደዚህ አመጣቸው ዘንድ ይገባኛል፤ ቃሌንም ይሰሙኛል፤ ለአንድ እረኛም አንድ መንጋ ይሆናሉ። "ስለዚህም፤ አብ ይወድደኛል፥ እንደ ገና አስነሣት ዘንድ እኔ ነፍሴን እሰጣለሁና። ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ ነገርግን እኔ በፈቃዴ እሰጣታለሁ፤ እኔ ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ እወስዳት ዘንድ ሥልጣን አለኝና፤ ይህንም ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ
ስለዚህም ነገር አይሁድ እንደገና እርስ በርሳቸው ተለያዩ። ከእነርሱም ብዙዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብዳል፤ ለምንስ ታዳምጡታላችሁ?” አሉ። ሌሎችም ይህ ነገር ጋኔን ከያዘው ሰው የሚገኝ አይደለም፤ ጋኔን የዕዉሮችን ዐይን ማብራት ይችላልን?” አሉ::

#መልእክታት
ቲቶ 1:5-12
ያዕቆብ 1:2-13
ሐዋ፡ሥራ 20:28-31

ምስባክ

       መዝሙር ፹፫ : ፮ – ፯

እስመ መምሕረ ሕግ ይሁብ በረከተ

ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል

ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

ትርጉም

የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።
ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።


ጥያቄ:- ትክክለኛውና እውነተኛው አምላክ ማን ነው? ይህ አምላክ መሓሪና ይቅር ባይ እንደሆነ በስፋት ይነገራል። መሓሪና ይቅር ባይ ነው ሲባል እንዴት ነው? ማለት አንድ ሰው ችግር ገጥሞት ፈጣሪዬ ሆይ አድነኝ ብሎ ቢማጸን ወድያውኑ ፈጥኖ ለምን አያድነውም? ልክ አንድ አባት ልጁ አደጋ ውስጥ ሆኖ በኀዘን አባቴ ርዳኝ ብሎ ሲማጸነው በፊት የበደለውን በደል ረስቶ ፈጥኖ እንደሚያድነው ፈጣሪም ለምን ፈጥኖ አያድንም 30 ወይም 40 ዓመት ለምን ዝም ይለዋል? ብዙ ጊዜ ስለማይጠቅመን ነው ወይም ጊዜ ስላልደረሰ ነው ወይም ስለኃጢአታችን ነው የሚል ምክንያት ይቀርባል። እንዲህ ከሆነ የፈጣሪ ደግነቱ የታለ? ስለማይጠቅመን ነው ቢባል ሌላው የሚጠቀምበት ጤና ለእኔ ለምን አይጠቅመኝም ጊዜው ገና ነው ቢባል አርባ አመት ሙሉ መልስ ያላገኘ ጥያቄ መቼ ያገኛል?

መልስ፦ የእግዚአብሔርን መሓሪነት የሰው ልጅ መርምሮ እንዲህ ነው እንዲያ ነው ማለት አይችልም። እነዚህን ጥያቄወች ለመመለስ መጀመሪያ የመኖርን ምክንያት ማወቅ ያስፈልጋል። ለምን እንኖራለን? መኖር ካለመኖር ብልጫው ምንድን ነው? መሞታችን ካልቀረ የመኖራችን ጥቅም ምንድን ነው? የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልጋል። በዚህ ዓለም ደስታ ብቻ ወይም ኀዘን ብቻ የለም። ደስታና ኀዘን፣ ጤናማነትና በሽተኛነት እየተፈራረቁ ይኖራሉ። ሰው በተለያየ ምክንያት ይታመማል። ከሕመሙ ለመዳን ወደ እግዚአብሔር ሊለምን ይችላል። እግዚአብሔርም ምላሽ የሚሰጥበት ወቅት አለ። ምላሽ የማይሰጥበት ጊዜም አለ። ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ በሽተኛ ነበር። በሽታውን እንዲያርቅለት እግዚአብሔርን ቢለምነውም እግዚአብሔር ግን በሽታውን አላራቀለትም (2ኛ ቆሮ.12፥7-10)። ቢታገሡት ሰማያዊ ዋጋን የሚያሰጥ በሽታ አለ። በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታም አለ። በኃጢአት ምክንያት ለመጣው ንስሓ ገብቶ ሥጋውን ደሙን መቀበል ነው። ስለዚህ ከእኛ የማይርቅ በሽታ ካለ ብንታገሥና እግዚአብሔርን ከማመስገን ባንከለከል ሰማያዊ ዋጋን የሚያሰጠን ስለሆነ ለእኛ ጥቅም ሲባል የመጣ በመሆኑ እግዚአብሔር አያርቀውም። በተረፈ በግምት እናውራ ካላልን በስተቀር የእግዚአብሔርን ፍርዱንና ይቅር ባይነቱን እኛ የመመርመር አቅሙ የለንም። እግዚአብሔር በመልክ፣ በፆታ፣ በቁመትና በመሳሰሉት ልዩ ልዩ አድርጎ ፈጥሮናል። አንዱን አጭር አንዱን ረጂም፣ አንዱን ጤነኛ አንዱን በሽተኛ፣ አንዱን ቀይ አንዱን ጥቁር ለምን ያደርገዋል እያልን ባለችን ትንሽ አእምሮ ለመተቸት መጣር አይገባም። ምክንያቱን የሚያውቀው እርሱ ራሱ ብቻ ነው። የሕመማችንን ምክንያት ራሱን እግዚአብሔርን ሳንጠይቅና ሳይነግረን ደግነቱን ዝቅ ያደርገዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ምናልባት ያ ሰው ጤነኛ ቢሆን የበለጠ ኃጢአተኛ የሚሆን ቢሆንስ? ለሰባ ሰማንያ ዓመት ጤነኛ ሆኖ ኃጢአተኛ ከሚሆን መቶ ዓመት በሽተኛ ሆኖ ገነት መግባት የተሻለ ነውና። እና እግዚአብሔርን በአካል አግኝተን ስለእያንዳንዱ ምክንያት ባልጠየቅንበት ሁኔታ የራሳችንን ድምዳሜ ወስደን ለመተቸት መሞከር አላዋቂነት ነው።


“ፍቅር የሕይወት ሰንሰለት፣ የነዳያን እናት፣ የባለጸጎች መምህር፣ የወላጅ አልቦች ተንከባካቢ፣ የአረጋውያን ጠባቂ፣ የምስኪኖች ሀብት፣ የተጎዱ ኹሉ የጋራ ወደብ ነው።'' ፍቅር ደግሞ ክርስቶስ ነው።

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

20 last posts shown.