ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ባለፈው የተቋረጠውን ትምህርተ ማህሌት ይቀጥላል፣ዛሬ ስለ ምልጣን እናያለን፤ ይከታተሉን።
@EOTCmahletምልጣን ማለት በ 2 ሰዎች የሚደርስ ስርዓት ሲሆን ምንጊዜም አንዱ መሪ አንዱ ተመሪ በመሆን ይደርሳል።
@EOTCmahletምልጣን ላይ ተመሪው ባዶ እጁን(መቋሚያን በማስቀመጥ) በመሪው የሚባልለትን በመድገም ይላል። መሪው ደግሞ ከተመሪው ኋላ በመሆን አንዳንዴ መስቀልን በመያዝ ሚባለውን ስርአት ያደርሳል።
@EOTCmahlet@EOTCmahlet፨ስርአተ ምልጣን(አንገርጋሪ)፦
ይህ እንደሚታወቀው ማህሌቱ ወደ መጠናቀቅ ሲሄድ ነው። ዲያቆናቱ የሌሊት ምስባክን ከሰበኩ በኋላ ወንጌል ተነቦ የሚቀርብ ነው። ምልጣን ከመባሉ በፊት #እስመ ለአለም በምሪት ዜማ ይባላልና አንድ ማህሌታዊ አገልጋይ መስቀሉን ከዲያቆን በመቀበል ሃሌ ሉያ በማለት ይጀምራል ተመሪውም ሃሌ ሉያ በማለት ይቀበላል።
@EOTCmahletእስመ ለዓለም በቅኝት
የማነ ብርሃን ኀደረ ኃበ ማርያም ድንግል፤ ጥዕምት በቃላ ወሠናይት ምግባራ ፤ እሞሙ ለሰማዕት፤ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፤ (ማንሻ)፦ እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን፤ መድኃኒት ኮነት ለኩሎ ዓለም
ሁሉም እስመ ለዓለሙን በዜማ ይቀበላሉ
🌿የምልጣን አባባል፦
ምልጣን ሃሌ ሉያ በማለት ይጀመር እንጂ ማንሻ አለው። ለምሣሌ አንዱን ምልጣን እንይ፦
@EOTCmahletምልጣን፦
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።
@EOTCmahletመሪ- ሃሌ ሉያ
ተመሪ- ሃሌ ሉያ
መሪ-ክነፈ ርግብ
ተመሪ-ክነፈ ርግብ
መሪ-በብሩር ዘግቡር
ተመሪ-በብሩር ዘግቡር
መሪ-ወገበዋቲሃኒ
ተመሪ-ወገበዋቲሃኒ
መሪ- በሐመልማለ ወርቅ
ተመሪ-በሐመልማለ ወርቅ
መሪ- አንቲ ምስራቅ
ተመሪ-አንቲ ምስራቅ
መሪ-ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ
ተመሪ-ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ
መሪ-አማን
ተመሪ-አማን
መሪ-ኪዳንኪ ኢየኃልቅ
ተመሪ-ኪዳንኪ ኢየኃልቅ
@EOTCmahletከዛ በዝማሜ ሃሌ ሉያ ተብሎ ይዘመምና ተመልሶ ወደ ማንሻ ይሄዳል። ዜማውም ረዘም ይላል።
በዝማሜ
👉 ሃሌ ሉያ ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።
@EOTCmahletመሪ፦አንቲ ምስራቅ
ተመሪ፦አንቲ ምስራቅ
መሪ፦ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ
ተመሪ፦ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤
መሪ፦አማን
ተመሪ፦አማን
@EOTCmahletከዛ < ኪዳንኪ ኢየኃልቅ > ምትለዋን ብቻ በዝማሜ ይባላል። ከዛ ወደ 3ኛ ሰው በመሄድ ከማንሻ ብሎ ያዜማል።
ንሽ
አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።
ከዛ ወደ 4ኛ ሰው በመሄድ ከማንሻ ያነሳል። ከ
@EOTCmahlet@EOTCmahletበመቀጠል "አማን በአማን ኪዳንኪ ኢየኃልቅ " የሚለው በዝማሜ ተብሎ ከጽናጽል ና ከከበሮ ጋር ይቀርባል
አባባሉም፦
በጽፋት የከበሮ አመታት ፩ ጊዜ
አማን በአማን ኪዳንኪ ኢየኃልቅ
ከዚያ በቁርቋሮ እና በጽፋት
አማን በአማን አማን በአማን .... ፩ዴ በቁርቋሮ
አማን በአማን ... ፩ዴ በጽፋት
ኪዳንኪ ኢየኃልቅ.... ፩ዴ በቁርቋሮ
ኪዳንኪ ኢየኃልቅ.... ፩ዴ በጽፋት
አመላለስ አባባል ፦
አማን በአማን አማን በአማን ኪዳንኪ አማን በአማን አማን በአማን /፪ ጊዜ/
ኪዳንኪ ኢየኃልቅ/፪ ጊዜ/
አመላለሱ ተብሎ እንዳለቀ በጽፋት የከበሮ አመታት
አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን በአማን ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።
ዝግ አባባል
አንቲ ምስራቅ አንቲ ምስራቅ /2 ጊዜ/
ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ አንቲ ምስራቅ /2 ጊዜ/
አማን በአማን ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።
ከዚ በኃላ በጽፋት
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።
ወረቡ እዚጋ ይባላል፦
ወረብ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ/፪/
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ ምሥራቅ ደብረ ሕይወት/፪/
በቁም አባባል
አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ
እስመ ለዓለሙን በቁም ብለው ይዘልቃሉ
እስመ ለዓለም፦
የማነ ብርሃን ኀደረ ኃበ ማርያም ድንግል፤ ጥዕምት በቃላ ወሠናይት ምግባራ ፤ እሞሙ ለሰማዕት፤ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፤ (ማንሻ)፦ እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን፤ መድኃኒት ኮነት ለኩሎ ዓለም
በመረግድ
እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ/2/ ቅቡፃን፤ መድኃኒት ኮነት ለኩሎ ዓለም/2/
በመረግድ 👉
የማነ ብርሃን ኀደረ ኃበ ማርያም ድንግል፤የማነ ብርሃን ኀደረ ኃበ ማርያም ድንግል፤ ጥዕምት በቃላ ወሠናይት ምግባራ ፤ጥዕምት በቃላ ወሠናይት ምግባራ ፤ እሞሙ ለሰማዕት፤ ወእኅቶሙ ለመላእክት፤ እሞሙ ለሰማዕት፤ ወእኅቶሙ ለመላእክት
በጽፋት👉
እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን፤ መድኃኒት ኮነት ለኩሎ ዓለም
አመላለስ ከተባለ በኃላ " የማነ ብርሃን" ብለው በጽፋት ይሉትና የኪዳኑን ሰላም ጸፍተው ወደ መዝሙር ያመራሉ
ስለ ስርዓተ አንገርጋሪ ይህ ካየን ይበቃል። በቀጣይ ስለ ዋዜማ አቋቋም እናያለን። ለወዳጅዎ ማጋራትን አትርሱ!
አስተያየት ካለ
👉
@eotcmahletawian👇👇🇪🇹
👉
@EOTCmahlet👈
👉
@EOTCmahlet👈
👉
@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@EOTCmahlet #Join & share