መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው አውዳሚ የእሳት አደጋ ወቅት አንዳንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን አባላት ከባለሱቆች ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁ፣ ከአንድ እና ከሁለት ሳይሆን 8 ሰዎች አረጋግጠውልኛል‼️
🗣Via Elias Meseret
በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ "ማንን ነው ምናናግረው?" በማለት ለረጅም ደቂቃዎች ማጥፋት እንዳልጀመሩ እነዚህ የአይን እማኞች ይናገራሉ።
"ማለት የፈለጉት ብር እንዲሰጣቸው ከማን ጋር ነው ምንደራደረው ነው። ይህ ነገር የተለመደ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ንብረት እስኪወድም ግን በዚ ደረጃ አይመስለኝም ነበር" ያለኝ አንድ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰብ ይህን መረጃ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደሚያውቁ ነግሮኛል።
መሠረት ሚድያ ደግሞ በደረሰው መረጃ በስፍራው ቀድመው በአምቡላንስ የደረሱ የእሳት አደጋ ቡድን አባላት 4 ሚልዮን ብር በመቀበል በድርድር ተስማምተዋል።
ብር ከፋዮቹ በጊዜው የነበሩ የሱቅ ባለቤቶች ሲሆኑ የብዙ ሚሊዮን ብር ንብረት ሱቆቹ ውስጥ ላይ ስለነበራቸው የተጠየቁትን ለመክፈል ምርጫ ስላልነበራቸው አላቅማሙም ነበር፣ ጠያቂዎቹ ደግሞ በጊዜው ቀድመው አምቡላንስ ይዘው የደረሱ የእሳት አደጋው ሰራተኞች ናቸው ተብሏል።
ይህን ድርጊት የፈፀሙት ሁሉም ሳይሆኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች መሀል የሚገኙ የሰው ንብረት ውድመት ሳይታያቸው እና ሙያቸውን የካዱ ጥቂቶች እንደሆኑ ይሰማኛል።
ጉዳዩን "ውሸት" ምናምን ብሎ ለማለፍ ሊሞከር ይችላል፣ የሚያዋጣው ግን አጣሪ ቡድን ወደስፍራው በመላክ እነዚህን አሳፋሪ ጥፋተኞች በህግ መጠየቅ ነው።
@Esat_tv1