'ከረሜላ ልስጥሽ' በማለት አታሎ የ9 ዓመት ህጻን የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት እስራት ተቀጣ‼️
በይርጋጨፌ ከተማ የ9 ዓመት ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።
ግለሰቡ ድርጊቱን የፈጸመው በቀን 10/9/2016ዓ.ም በግምት ከጥዋቱ 4 ሰዓት በይ/ጨፌ ከተማ ካራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ነው።
የግል ተበዳይ 9 ዓመት ህጻን ተማሪ ስትሆን ሜክ አፕ ተጠርታ ተምራ እየመጣች ባለችበት ቅ/ኪዳነምህረት ት/ቤት ፊት ለፊት ባለው የመጠጥ ማከፋፈያ ውስጥ ሆኖ እማ ነይ ከረሜላ ልስጥሽ በማለት ደስታ ከረሜላ የመሰለ ነገር እንደበላች እራሷን እንደሳተች የክስ መዝገቡ ያስረዳል።
በመቀጠልም ወደ ውስጥ በማስገባት በፒላስቲክ ጅባ ላይ አስተኝቶ አሰገድዶ የደፈረ መሆኑንና ተከሳሽ ሆን ብሎ አስቦ በማድረጉ ተገልጿል።
ተከሳሹ፥ 1997 ዓ.ም በሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ዕግ አንቀፅ 627/1 የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀመው በሕፃናት ልጆች ላይ በሚፈፀም በግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።
በዚህም ተከሳሹ 14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉን የይርጋጨፌ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
@Esat_tv1