እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ካቆመች ጀምሮ ከ1 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን መገደላቸዉ ተገለጸ‼️
ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ በጋዛ እና አከባቢዉ ላይ 1መቶ ፍልስጤማዊያን መገደላቸዉ ተዘግቧል፡፡
እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ካቆመች በኋላ ባደረሰችዉ ጥቃት የሞቱ ፍልስጤማዊያን ቁጥር 1ሺህ 1መቶ 63 ደርሷል ተብሏል፡፡
እንደ ፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር ከሆነ በጥቅምት 7 በተጀመረዉ ጦርነት ህይወታቸዉ ያለፉ ፍልስጤማዊያን ቁጥር 50ሺህ 5መቶ23 ደርሷል፡፡
ደህንነቱ የተጠበቀ ነዉ በተባለዉ በምዕራብ ካን ዩኒስ በሚገኘዉ አል-ማዋሲ የስደተኞች መጠለያ ዉስጥ የነበሩ ተፈናቃይ ፍልስጤማዊያን የእስራኤል የዓየር ጥቃት ኢላማ መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በጋዛ ከተማ በሚገኝ አንድ መንደር ላይ ባደረሰችዉ ሌላ ጥቃት 9 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ፤ 15 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚመራ ክሊኒክ ላይ ባደረሰቸዉ እና 70 ሰዎች በተገደሉበት ሌላ ጥቃት ብዙ ህጻናት ሲገደሉ የፖሊስ አባላትም ህይወታቸዉ አልፏል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡
@Esat_tv1