Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በፖሊስ ተሽከርካሪ ውስጥ ሆኖ ብር ሲቀበል በቪዲዮ የታየ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ኢንስፔክተር ኤርሚያስ ኤርጌኖ የተባለው የፖሊስ አባል በፖሊስ ተሽከርካሪ ውስጥ ሆኖ ሁለት መቶ የብር ኖት ሲቀበል የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ መዘዋወሩን መነሻ ባደረገ መረጃ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ አባሉ በተሽከርከሪ ውስጥ ተቀምጦ ሪሲቲ እየሰጠ የ200 ብር ኖት ጉቦ ሲቀበል የሚያሳይ ነው፡፡
በፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዩን የሚያማርሩ እና የተቋሙን መልካም ገፅታ ከሚያበላሹ ህገ-ወጥ ተግባራት ውስጥ ጉቦ መቀበል አንዱ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ፤ መሰል ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈፅሙ አመራርም ሆነ አባላት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት መብታቸውን በገንዘብ የሚገዙም ሆነ ህገ-ወጥ ተግባር ፈፅመው ጉቦ በመስጠት ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚሞክሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ያሳሰበው ፖሊስ ብልሹ አሰራርን ለማጋለጥ በተለያዩ አግባቦች መረጃን የሚሰጡ አካላትን በማመስገን በቀጣይም መረጃዎችን በማድረስ የህብረተሰቡ ተባባሪነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አሰእተላልፉዋል።
@Esat_tv1