አምላክ ተወልዷል የሚለው ሀሰብ የዘቀጠ መሆኑ ጥርጥር የለውም።ኢማም ኢብኑ ሀዘም ስለ ስላሴያቸው ሲናገር “ወላሂ አላህ በቁርአን ውስጥ ባይነግረኝና ተገናኝቼ ባላናግራቸው ኖሮ እንዲህ የሚል ትውልድ ይኖራል ብዬ አላስብም" ማለቱ ይታወቃል እኔም ጌታ ተወልዷል የሚለውን ሀሳብ “ወላሂ አላህ በቁርአን ውስጥ ባይነግረኝና ተገናኝቼ ባላናግራቸው ኖሮ እንዲህ የሚል ትውልድ ይኖራል ብዬ አላስብም"ስል እምነታዊ ቃሌን እሰጠለሁ! እስቲ አስቡት ከ tiny atom እስከ Giant polymer ድረስ የፈጠረ God? ደቂቅ ህዋሳትን የፈጠረ አምላክ፤ አስደናቂውን የሰውን ልጅ ያስገኘ አምላክ፤ ምድርን እና ሰማይን የፈጠረ አምላክ፤ ፕላኔቶችን ክዋክብትን ጋላክሲዎችን በጥቅሉ ይህን አጽናፈ አለም ያለ እንከን ያስገኘ አምላክ እንዴት ሴት ልጅ አምጣ ወለደቹህ ይባላል? ያኔ ኢብኑል ቀይም "አኡባደል መሲህ ለና ሱአሉን ኑሪዱ ጀዋበሁ ሚመን ወአሁ” በሚል የግጥም መክፈቻ ጥያቄዎቹን እንደደረደረው እኔም "የመሲህ ባሮች ሆይ ጥያቄ አለን -የተረዳ ካለ መልስ እንፈልጋለን ” ስል How? እንዴት?እኮ እንዴት? ፍፁም የሆነው አምላክ ቅዱስ የሆነው አምላክ በከብት በረት ውስጥ እንዴት ማህፀን በርግዶ ወጣ ይባላል?