ጥምቀት ለኛ ድምቀት ወይስ ጥፋት?
ጥምቀትን ተያይዞ አንዳድ ሙስሊሞች የሚያደርጉትን ገደብ ያጣ ሽር ጉድ አንድም "ልወደድ ባይነትን" ከመፈለግ ሲሆን ሁለትም "ወሎዬነት እንዲህ ነው"ሲሉ ለመስበክ ነው። በትክክል እነሱ እንደሚሉት ወሎ ስትሆን ለክርስትያን በዓል ምታሽቃበጥ፣ ታቦት በፍቃድህ የምትከተል ፣በመጨረሻም ታቦቱ ሲገባ "አልሀምዱሊላህ " የምትል ከሆነ ወሎነት ይቅርብን የሚሉ በዙ እልፍ አዕላፍ ሙስሊም ወልዬዎች እንደሚኖሩ ሸክም በለው ጥርጥር ኢንጅሩ (የለውም)! በመሰረቱ ኢስላም የራሱ የሆነ ህግና መርህ አለው ከሌሎች እምነት ባልተቤቶች ጋር ትስስርህ እንዴት መሆን እንዳለበት በቁርአን በተጨማሪም በሱናው ውስጥ ተቀምጦልሃል!በመልካም ነገር ትተባበረዋለህ፤ ሲታመም ሄደህ ትጠይቀዋለህ፤ ሲቸግረው ትረደዋለህ ፣ሲርበው ታበላዋለህ፣ ከዚህም ባለፈ የጉርብትና ሀቅ እንዳለው መርሳት እንደሌለብህ እንዲሁም ዘመድህም ከሆነ የዝምድና ሀቅ እንደሚኖረው ያስተምረሃል!በዚህ መልኩ እስልምና አስቀምጦት ሳለ ከዚህ ባለፈ መጋገጥ ግን አግባብነት የሌለው ብቻ ሳይሆን አስመሳይነት ነው። እንዴት አስመሳይነት ይሆናል ብሎ ለሚጠይቅ አጥብቆ ጠያቂ ምላሼ የሚሆነው የማታምነውን ነገር ማወዳደስ ማደናነቅ እና ለሱ ማጨብጨብ በአማኞቹ ለመወድድ እያደረከው ያለው ማስመሰል ነው ስል እንቅጩን ነግርሃለሁ!ወሎ ይቻቻላል በሚል ስም ጥምቀትን ማወዳደስ እንዲሁም የምትከተለውን ሀይማኖት በሚፃረሩ በዓላት ላይ ድቤ መደለቅ ጥቅም የለውም ብቻ ሳይሆን ሀጥያት ነው!ሀጥያቱም በሰዎች ለመወደድ ሲባል አላህ(ሱ:ወ) የሚጠላውን ድርጊት ላይ ተባባሪ በመሆን ነው።
ከዚህ በላይ ክስረት አለን?ዱንያዊ ክስረት!አኺራዊ ክስረት!አላህ ይጠብቀን!