ኡቡንቱ ( humanity to others )
ይህ ሰው አንትሮፖሎጂስት ነው ። እና ከስራው መልስ በአንድ በደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል በሚገኝ ትንሽ መንደር አረፍ ብሎ እያለ ፡ እነዚህ ትናንሽ ልጆች ይመጡና ቆመው ያዩታል ።
ሰውየው ልጆቹን ሲያይ አንድ ጫወታ ሊያጫውታቸው ፈለገ ።
እናም የፍራፍሬ ቅርጫቱን ወስዶ ዛፍ ጥግ አስቀምጦ እነሱን የተወሰነ ሜትር አርቆ አስቆማቸው ። አሁን አለ. .. ከናንተ መሀል በፍጥነት በመሮጥ ዛፉ ጋር ቀድሞ የሚደርሰው ልጅ ፡ በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ በሙሉ ለብቻው ይወስዳል አላቸው ።
ልጆቹ ተስማሙ ።
ጀምሩ አላቸውና ፡ ከነሱ መሀል የትኛው ልጅ ቀድሞ ደርሶ ፍራፍሬውን እንደሚወስድ ለማየት ራቅ ብሎ ቆመ ።
ልጆቹ ጀምሩ ሲባሉ ፡ ቀድሞ ለመድረስ ከመሮጥ ይልቅ እጅ ለእጅ ተያይዘው ፡ በእኩል እርምጃ የፍራፍሬው ቅርጫት ወደተቀመጠበት ዛፍ አመሩ ።
እኩል ደርሰውም የፍራፍሬውን ቅርጫት አንስተው እኩል ተካፈሉ ።
ያላሰበው ነገር ያጋጠመው አንትሮፖሎጂስት ፡ ታዳጊዎቹን በአድናቆት እያየ ፡ አንዳቸው ቀድመው ደርሰው ፍራፍሬውን በሙሉ እንደመውሰድ ፡ ለምን በህብረት መጓዝ እንደፈለጉ ጠየቃቸው ።
የታዳጊዎቹ መልስ UBUNTU የሚል ነበር ቃሉ የአፍሪካ ቃል ስለሆነ ብዙ አልተረዳም ነበርና እንዲያብራሩለት ጠየቀ ።
ልጆቹ እንዲህ አሉት. ...
ከመሀከላችን አንዱ ብቻ አግኝቶ ቢደሰት እና ሌላው በማጣቱ ቢያዝን ምን ይጠቅመናል ?
@Celebrity_ET