የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጎፋ ዞን ኡባ ደብረፀሐይ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ የመስክ ምልከታ አደረገ
የመስክ ምልከታው ዋና ዓላማ የማህበረሰብ ብሮድካስቶች በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል፣ በአሰራር፣ በይዘት፣ በፋይናንስ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው ከመስራት አንጻር ያሉበትን ደረጃ በመገምገም፤ ውስንነቶችን በመቅረፍ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እንዲቻል ለማድረግ መሆኑን የመስክ ምልከታ ቡድኑ አስተባባሪ በባለሥልጣኑ የማህበረሰብና የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ክትትል ም/ዴስክ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሻንቆ ገልጸዋል።
አቶ ሁሴን አያይዘውም በምልከታው ወቅት በማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያው የተለዩ ክፍተቶችን መፍትሔ እንዲያገኙ ከቦርድ አመራሮች፣ ከአካባቢው አስተዳደር አካላት እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ መቻሉን ገልፀው የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያውን የሚያጠናክር የአድማጮች ቡድን በማደራጀትና በቀጣይ በሚከናውኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት መደረጉን አክለው ተናግረዋል።
በመስክ ምልከታው በጣቢያው ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች በማህበረሰብ ብሮድካስት አገልግሎቶች ጽንሰ ሐሳብ፣ ተልዕኮዎች፣ ተግባርና ሃላፊነት እንዲሁም በጋዜጠኝነት ሙያና የስነ ምግባር መርሆዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱም ተገልጿል።
በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል