የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት “የህዝባዊ ቁጣ መገንፈል እና ተዛማጅ ጉዳዮችን” ሊያስከትል እንደሚችል ኢህአፓ አስጠነቀቀ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ያለው እና ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ የተሸጋገረው የኮሪደር ልማት፤ የከተማይቱን ነዋሪዎች “ሰብአዊ መብቶች የጣሰ ነው” ሲል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ዛሬ በሰጠው መግለጫ ወቀሰ። በኮሪደር ልማቱ ሳቢያ“እያየለ የመጣው የህዝብ ብሶት እና ምሬት” በቸልታ ከታለፈ፤ “የህዝባዊ ቁጣ መገንፈል እና ተዛማጅ ጉዳዮችን” ሊያስከትል እንደሚችልም ፓርቲው አስጠንቅቋል።
አዲስ አበባ “ዓለም አቀፍ ደረጃዋን ጠብቃ የመልማቷ ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ” እንዳልሆነ በዛሬው መግለጫ የጠቀሰው ፓርቲው፤ ይሁን እንጂ የከተማዋ ልማት እና እድገት “ከኗሪው ህዝብ መብት መከበር” እና “ከጥቅሞቹ መጠበቅ” ተነጥሎ ሊታይ እንደማይገባ አሳስቧል። ልማቱ “ከዜጎች አጠቃላይ የኑሮ መስተጋብር እና የኢኮኖሚ እድገት ጋር የተጣጣመ” መሆን እንደሚኖርበትም ፓርቲው በአጽንኦት አንስቷል።
የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የኢህአፓ የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ አካሉ፤ በከተማይቱ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት “የበርካታ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶች፣ አነስተኛ እና ከፍተኛ የንግድ ድርጅቶች” መፍረሳቸውን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየወሰዳቸው ያላቸው እርምጃዎች “የነዋሪዎች ሁኔታ ያላገነዘቡ፣ ምቹ ጊዜን ያልጠበቁ እና ከግምት ያላስገቡ” መሆናቸውንም አመልክተዋል።
((እኛም ህዝባዊ አመፁ የማይቀር ነው እንላለን))