ተነሳሽነትን የሚጨምሩ 5 ነጥቦች
Get lifted with motivation
---------------------------------
የሰው ልጅ አንድን ነገር ለመስራት ተነሳሽነት ያስፈልገዋል፤ ይሄ መነሳሳቱ ውጫዊም (Extrinsically motivated) ሆነ ውስጣዊ (Intrinsically motivated) ስራን ለመጀመር፤ ጀምሮም ከፍጻሜ ለማድረስ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ታዲያ በህይወታችን ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘውን ይህን እሴት እንዴት ነው ማዳበር የምንችለው? ለዚህ ይረዱናል የተባሉ 5 ነጥቦች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
• ማበረታቻዎችን በጥንቃቄ መጠቀም
ከአንድ ክንውን በኋላ እራሳችንን የምናበረታታበት መንገድ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል ምክንያቱም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ስኬቶች እራሳችንን የምንሸልም (ቃላዊ ወይም ቁሳዊ ማበረታቻ) ከሆነ ለአዲስ ነገሮች አይጋብዘንም፡፡
• አስቸጋሪውን እና አዲሱን መንገድ መምረጥ
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የሰራነውን እና ያደረግነውን ነገር፤እንደገና በድጋሜ ለመስራት መነሳት ተነሳሽነታችንን አይጨምረውም እንደውም ጭራሽ በማጥፋት ስልቹ ያደርገናል፡፡ ስለዚህ ያልሞከርነውን እና አስቸጋሪ የሚመስለንን ነገር ከመሞከር ወደ ኋላ ባለማለት ተነሳሽነትን መጨመር እንችላለን፡፡
• ስኬትን አስቀድሞ አለማለም
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲባል እንደነበረው የመጨረሻውን ስኬት አስቦ ወይም አልሞ ወደ ተግባር መግባት ተነሳሽነትን እና ትጋትን ይጨምራል የሚል እሳቤ ነበር፤ በቅርብ የወጡ የጥናት ጽሑፎች እንዳመለከቱት ከሆነ ስኬትን ቀድሞ ከማለም በመቆጠብ ድርጊቱን ስናከናውን በስኬት ለማጠናቀቅ ምን ዓይነት መሰናክሎች እንደሚያጋጥሙን እና እንዴት እንደምናልፋቸው መንገዶችን መቀየስ ተነሳሽነትን ይጨምራል፡፡
• በቡድን ውስጥ ተደማጭነትን መጨመር
ስራዎች በቡድን ሲሰሩ እያንዳንዱ አባል የሚሰጠው አስተዋጽኦ በተገቢው መንገድ የማይታይ ከሆነ የግለሰቡ ተነሳሽነት ይቀንሳል፡፡ ስለዚህም የቡድን ስራ ሲሰራ የእያንዳንዱ ግለሰብ ድምጽ ሊሰማ እና ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል፤ ካልሆነ የአባሉ ተነሳሽነት ይቀንሳል፡፡
• ከመድረሻው ይልቅ መንገዱ ላይ ትኩረት መስጠት
ፍጻሜያችን የቱጋ ነው ? ይሳካልኝ ይሆን ወይስ አይሳካም ? ብሎ ከመብሰልሰል በመንገዳችን ላይ በሚያጋጥሙን አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤቶች ልምድ እየቀሰሙና እና እየተማሩ ወደ ፊት መጓዝ፡፡
@EthioBini @EthioBini