የክረምት ከሰል እና የጤና መዘዙ
በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ
ከሰል ምግብ ለማብሰል፣ ሙቀት ለማመንጨት እና ለተለያዩ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ያገለግላል።
ይሁን እንጂ ከሰል በጣም ብዙ የጤና መዘዝ እንዳለው ይታወቃል። በክረምት ከሚጋጥሙን አሳዛኝ የህክምና ክስተቶች ውስጥ ዋናው በከሰል ጭስ መታፈን፣ መመረዝ እና መሞት ነው።
በክረምት ቤትን ለማሞቅ ከሰል አይጠቀሙ። ምንአልባትም መጠቀም ካለብዎት በር እና መስኮት መክፈት አይርሱ። ከሰል ጭሱ ከጠፋ ችግር የለውም በማለት አይዘናጉ። ከሰል ቤት እንዲሞቅ ለማድረግ ሲሉ ብዙ የዋህ ነፍሳትን አጥተናል።
ከሰል መርዝ መሆኑን ገዳይ መሆኑን ለአፍታ አይርሱ ሲጠቀሙ ከቤትም ከበርም ያርቁ።
ለመሆኑ ከሰል የሚያደርሰው የጤና እክል ምንድን ነው?
1. የመተንፈሻ አለርጂ መቀስቀስ /የመተንፈሻ አካል መበሳጨት /
2. የካርበን ሞኖ ኦክሳይድ ብክለት እና መመረዝ አስከ ሞት ያደርሳል።
3. የነርቭ ስርአት መዛባት ፡ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ፡ መነጫነጭ ፡ የእንቅስቃሴ ስርዓት መዛባት
ከሰል የሚለቀው አየር ካርበን ሞኖ ኦክሳይድ እጅግ ለህይወት አስጊ ከሚባሉት የአየር አይነቶች ይመደባል። በሚቀጥለው ቀን በዝርዝር እመለስበታለሁ። መልካም አዳር። ደግሞ የዓለም ስጋት የሆነውን ኮሮና መከላከል አይርሱ። ከየትም ከማንም በተለይ ከቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ እንደሚይዘን አይርሱ። እንጠንቀቅ እንጠበቅ።
@EthioBini @EthioBini