በናይጄሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በደህንነት ችግር ከ600 ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ
ከግንቦት 2023 እስከ ሚያዚያ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ በናይጄሪያ ከ600 ሺ በላይ ሰዎች በፀጥታ እጦት መገደላቸውን የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ (NBS) መረጃ ያሳያል። ይፋ የተደረገው መረጃ በመጠለፉ ሪፖርቱን ለመመልከት ሰዎች ተቸግረው ነበር። በሀገር አቀፍ ደረጃ ግን ከ614 ሺ 9 መቶ 37 ያላነሱ ሰዎች በሰላም መደፍረስ ተገድለዋል።
በሰሜን ምእራብ ናይጄሪያ ከፍተኛ የሰዎች ሞት የተመዘገበ ሲሆን ከ206 ሺ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ 188 ሺ ሰዎች ግድያ ሲመዘገብ በደቡብ ምዕራብ ናይጄሪያ ዝቅተኛ የተባከው የ15 ሺ 6 መቶ 93 ሰዎች ሞት ተመዝግባል። ለቁጥሩ ከፍተኛ ምክንያቱን ለይቶ መናገር ባልችልም መረጃው ትክክል መሆኑን አረጋግጣለሁ ሲሉ የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ ቃል አቀባይ ሰንዴይ ኢቼዲ ተናግረዋል።
የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ አክሎም 2 ሚሊዮን 235 ሺ ናይጄሪያውያን ታግተው በድምሩ 1 ቢሊዮን 438 ሚሊዮን ገንዘብ ለቤዛ ወይም ታጋቾችን ለማስለቀቅ ተከፍሏል ብሏል። ናይጄሪያ በተለያዩ ክልሎች በርካታ የጸጥታ ችግሮች ገጥሟታል። ሀገሪቱ በሰሜን ምስራቅ የቦኮ ሃራም ሽፍቶች እየተዋጋች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ በሰሜን ምዕራብ በኩል ደግሞ የሽፍታዎች እና የታጣቂዎች አፈና ከፍተኛ ሆኗል።