📍ስለነገ ሳስብ አዝናለሁ። ዛሬ የሚሆነው ሁሉ ከአቅማችን በላይ እንደሆነ እናስባለን አይደል? መራሩ እውነት ግን ነገ ይብሳል። በአለማችን ብዙ የመከራ ድግስ ተደግሷል። እንደግለሰብ የተወሰኑ ግለሰቦች ህይወት ነገ ከዛሬ ሊሻል ይችላል ግን ብዙሀኑ የአለም ህዝብ ነገው ከዛሬ የከፋ ነው። ለዚህም ነው አዲስ የሚወለዱ ልጆች የሚያሳዝኑኝ።
የተፈጥሮ ውጤቶች ሆነን ሳለን አኗኗራችን ከተፈጥሮ ተቃራኒ ሆኗል። ወንድ እንደወንድ መሆን እያቃተው ነው፤ ሴት የሴትነት ወጉን እየተነፈገች ነው። በማንም አልፈርድም ማትሪክሱ ነው ዋናውን ሚና የሚጫወተው። የሰው ልጆች ከጤናማ የጊዜ ፈሰስ በላይ በሆነ ፍጥነት እንዲሰሩ ይገደዳሉ። ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን እንዲሁም ልጆች እና ወዳጆጃቸውን የሚንከባከቡበት በቂ ጊዜና የአእምሮ ትኩረት እያጡ ነው።
🌖የምንረግጣት ምድር ፍሬ አላፈራ ያለች ይመስል፤ ጤናችንን የሚጎዳ ሰው ሰራሽ አትክልት ፍራፍሬና ምግቦች ያውም በውድ ገዝተን ነው ብዙዎቻችን እንድንበላ እየተደረግን ያለነው። የምንወጋው መርፌ፤ የምንውጠው ኪኒን ከምን እና ለምን እንደተሰራ ብዙዎች አናውቅም። በዘመናዊነት ውስጥ የተደበቀችውን ጸረ-ሰብዕ መርዝ አናይም። በነጻነት ስም የሚጠመጠምብንን የእስር ሠንሠለት አናይም።
ሰብዓዊነት እንዲመናመን ለዘመናት ተሰርቱዋል- እነሆም ፍሬው ጎምርቱዋል። ነገን ስናስብ ዛሬን ከልብ በነገሮች ሁሉ አመስጋኝ ሆኖ መኖር ብልህነት ነው። ትውልዱ ቀልቡ በቁሳቁስ እንዲሸፍት ተደርጓል። በየInstagramu በሚታየው አርቴፊሻል ውበት የወንዱ ልብ ይሸፍታል፤ የሴቱ ልብ ኢንሴክዩርድ (insecured) ይሆናል። በየሚዲያው በሚታዩ ፊልተርድ በሆኑ መልከኞች ባለትዳሩ ቀልቡ ይሸፍታል፤ የትዳር ተጓዳኙ ውበት አልታይ ይለዋል።
🌗በላባቸው ሰርተው የሚኖሩ ታታሪ ወገኖች ሁልጊዜም ውድ ልብስ ለብሰው ፎቶ ሲለጥፉ ከሚውሉ ሰዎች ራሳቸውን እያወዳደሩ እድለቢስነት ይሰማቸዋል። ነገሩ እድል ብቻ አይደለም የአንዳንድ ሰዎች ስኬት መሰረቱ ህሊናን መሸጥ ነው። ምንም እንኳ ብዙሀኑ ለፍቶ አደር የሚገባውን የሚያገኝበት ሲስተም ውስጥ ባንሆንም እንኳ ህሊናቸውን ሸጠው የበላይነትን ከተቆናጠጡ ግለሰቦች ራስን ማወዳደር ፈጽሞ ልክ አይደለም፤ ቢያንስ ለፍቶ አደሩ በአንድ እነሱ በሌላቸው ከሁሉ የላቀ ሀብት ይበልጣቸዋል - ንጹህ ህሊና።
💫የነገን ለነገ ትተን የዛሬን እንዲህ ማድረጉ የተሻለ ይመስለኛል። በነገር ሁሉ ማመስገን- በማመስገን ውስጥ ብርታት ይገኛል፤ ሀዘን እና ጭንቀት ይቀንሳል እናም መልካም መንፈስ ይቀርበናል። በፈተና ሁሉ ነገሮችን የምንቋቋምበት አቅም እንዲኖረን ራስን ማዘጋጀት እንጂ ፈተና እንዳይኖር ማድረግ አይቻልም። ሌላው ለፍላጎቶቻችን ገደብ ማበጀት( እንደቤት እንጂ እንደጎረቤት አለመኖር) በቡድሂዝም አስተምሮት ከዋነኞቹ Four noble truths መሀል Nirodha የሚባል አለ።
Desire is the mère source of suffering, It is possible to end suffering by letting go of craving and attachment. This state of liberation is called Nirvana (Nibbana), a state of perfect peace and freedom from all suffering. ማለት ነው። እኛ ግን ሙሉ በሙሉ ከdésire or attachement መላቀቅ ስለሚከብደን boundary በማበጀት ስቃይን መቀነስና ሰላምን መጨመር እንችላለን።
📍ከአቅማችን በላይ የሆኑ ነገሮች ስለሌሉን የምናዝን ከሆነ በአቅማችን ያገኘናቸው በረከቶች ደስታን አይሰጡንም። ዋነኛው ትኩረታችን ለመኖር የሚያስፈልጉንን መሰረታዊ ነገሮች ለማሟላት መጣር፤ ሲሟሉም እለት እለት እያመሰገኑ ባሉን ነገሮች ደስታን ለማግኘት መሞከር ቁልፍ የደስታ ሚስጥር ነው። ይህ ማለት ግን የተሻለ ለማሳካት ጥረት ማድረግ የለብንም ማለት አይደለም። እንደ Maslow hiérarchie of needs ቅደም ተከተሉን ልንጠብቅ ይገባል ማለት እንጂ።
✨ሁሉን በአንዴ ለማሳካት የምንጥር ከሆነ ግን በማያቋርጥ ወሰን አልባ ጭንቀት እና እርካታ ማጣት ውስጥ እንናውዛለን ለዚህች አጭር ህይወት። ሌላው ፍቅር ነው። ከpossession የጸዳ ማፍቀርን መለማመድ ሌላው የቀና መንፈስ ቁልፍ ነው። ማንኛውንም ፍጡር መልካም ጎን ባየን ቅጽበት ሁሉ እንውደድ።
🔑ማትሪክሱ እርስ በእርስ እንዳንዋደድ እና ከመተባበር ይልቅ በፉክክር መንፈስ ጠላት እንድንሆን ነው እያደረገን ያለው። ስለዚህ ጥላቻን በፍቅር እናሸንፈው፤ ፍቅር የራስ የሆነን ነገር ብቻ ማፍቀር አይደለም። ማንኛውንም ሊፈቀር የሚገባ ነገር ሁሉ በማፍቀር በሌሎችም ሆነ በራሳችን ልብ ውስጥ ቀና መንፈስን መዝራት ማለት ነው።
✍የቃላት ቤት
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot