🛑በደስታ እና በሀዘን መሀል አንድ ድልድይ አለ ሰላም። ሰላም ከሁሉ ይልቃል የህይወት ሚዛን ነውና። ደስታም ሆነ ሐዘን ወጀብ ናቸው - በዓይነት የተለያዩ ህመሞች። ሰላም ከነዚህ ሁለቱ ኋላ የሚመጣ ስክነት ነው። ሌላ ወጀብ እስኪመጣ የሚሰማን ዘላለማዊነት። በፊዚክስ ውስጥ የሚዛናዊነት (የEquilibrium) ጽንሰ ሀሳብ ማዕከላዊ ነው። አንድ ስርዓት በውጫዊ ኃይሎች ቢገፋም እንኳ ወደ መጀመሪያው ሁኔታው ወይም ወደ አዲስ የተረጋጋ ሁኔታ የመመለስ ዝንባሌ አለው።
📍ሐዘን እና ደስታ በሰው አእምሮ ውስጥ የሚሠሩ ተቃራኒ ኃይሎች ተብለው ሊታዩ ይችላሉ። ደስታ ወደ ላይ የሚገፋ (ተነሳሽነትን የሚጨምር) ኃይል ሲሆን ሐዘን ደግሞ ወደ ታች የሚጎትት (ጉልበትን የሚቀንስ) ኃይል ነው። ሰላም ደግሞ እነዚህ ሁለቱ ኃይሎች እርስ በርስ ሲጣፉ የሚፈጠር የተጣራ ዜሮ ኃይል (Net Zero Force) ሁኔታ ነው። ነገር ግን ይህ ዜሮ ማለት እንቅስቃሴ የለም ማለት ሳይሆን ሚዛኑ ተለዋዋጭ (Dynamic) ነው ማለት ነው። ልክ እንደ አንድ አቶም ያለማቋረጥ በሚንቀሳቀሱ ኤሌክትሮኖች ዙሪያ ባለው ቋሚ ምህዋር ውስጥ እንዳለ መረጋጋት ነው።
🔷ሰው ደስታን ሲያሳድድ ጤናውን፣ ገንዘቡን፣ ህሊናውን፣ በዙሪያው ያሉ ወዳጆቹን እና ራሱን ያጣል። ደስታን በእጅጉ የሚያሳድድ ሰው በእጅጉ ሰላም ያጣ ሰው ነው- ሰላም ማጣት ትልቁ የሀዘን አይነት ነው። አዕምሮን የሚያልፍ ሰላም ነው ትልቁ ደስታ፣ ትልቁ ስኬት፣ ትልቁ አሁናዊነት። ይህም መገኛ ምንጩ ሚዛናዊነት ነው። በማንኛውም mental state ውስጥ ብንሆን balanceን እንፈልግ።
በቴርሞዳይናሚክስ ሚዛናዊነት ማለት ኢንትሮፊ (Entropy- የስርዓት መበታተን/ውዥንብር) ከፍተኛ ሲሆን እና የኃይል ፍሰት መቆም ማለት ነው። የሰው ልጅ ደስታን ማሳደድ የአዕምሮን ኢንትሮፊ ይጨምራል - ሚዛን የለሽ ጥረት፣ ጭንቀት፣ ጤናን ማጣት።
♦️ሰላም ደግሞ ይህ የውስጥ ውዥንብር የሚቀንስበት እና አእምሮ ወደ ዝቅተኛው የኃይል ሁኔታ ወይም Lowest Energy State የሚደርስበት ሁኔታ ነው። ሰላም ከፍተኛውን የውስጥ ሥርዓት ይፈጥራል፣ ይህም ከፍ ያለ የህሊና ብቃት እና ጤና ያመጣል።
ይህ የፊዚክስ ዋና መርህ ነው። ኃይለኛ የስሜት ፍንዳታን (Explosion) ለማስወገድ፣ በደስታም ሆነ በሐዘን ጊዜ የመለስተኛነት መርህ/ በመጠኑ መሆን (Principle of Moderation) አስፈላጊ ነው።
ልክ አንድ መሐንዲስ ድልድይ ሲሠራ ከፍተኛውን ሸክም እና ንዝረትን የሚቋቋም ሚዛናዊ ንድፍ እንደሚጠቀም ሁሉ የውስጥ ሰላምም ከሁለቱም ከፍ ያለ ደስታ (Peak Joy) እና ከባድ ሀዘን (Deep Sorrow) የሚመጣውን ድንጋጤ የሚከላከል መዋቅር ነው። ሁሉም ዋና ዋና ሃይማኖቶች እና መንፈሳዊ ፍልስፍናዎች ሰላምን ከውስጥ ሚዛን፤ ከአመስጋኝነት እና ከራስን ከታላቅ ኃይል/መለኮት (energy) ጋር ጋር ያገናኙታል።
♦️በምስራቃዊ ሃይማኖቶችና ፍልስፍናዎች (ቡዲዝም፣ ታኦይዝም፣ ሂንዱይዝም) ሰላም የሚገኘው የዓለምን ሥርዓት (Dharma/Tao) በመቀበል ነው፤ ይህም ሰላም እንደ ሥርዓተ ኮስሞስ (Cosmic Order) ነው የሚመለከቱት። በቡዲዝም ሐዘን እና ደስታ እንደ Dukha ወይም የስቃይ ምንጮች ይታያሉ። ሰላም ወይም ኒርቫና ደግሞ ከምኞቶች (የደስታ ፍለጋን ጨምሮ) መገደብ እና መላቀቅ (Detachment) የመጣ ነው ብለው ያምናሉ።
በታኦይዝም ታኦ (Tao) የሁሉ ነገር የመጨረሻው መርህ ነው - ፍፁም ሚዛን። የ ዪን እና ያንግ Yin and Yang ጽንሰ ሀሳብ እንደሚያሳየው፣ ደስታ (ያንግ - ብርሃን) እና ሐዘን (ዪን - ጨለማ) እርስ በርስ የተያያዙ እና የሚደጋገፉ የሕይወት ክፍሎች ናቸው። ሰላም የሚገኘው እነዚህን ተቃራኒ ኃይሎች እንደ ወጀብ በመመልከት ሳይሆን እንደ የአንድ ሙሉ አካል በመቀበል ውስጥ ነው። አመስጋኝነት ወይም Gratitude የውስጥ ሚዛንን የሚጠብቅ መንፈሳዊ መልሕቅ (Anchor) ነው። አሉታዊ አስተሳሰቦችን ይቀንሳል እና የራስን ዋጋ ከውጫዊ ስኬት ይልቅ በውስጣዊ በረከት ላይ ያኖራል ይህም ከጤና እና ከሰላም ጋር የተያያዘውን የሕይወት ትልቁ ስኬት ሚዛን ያጠናክራል።
📍በጣም ደስ የሚያሰኝ ሁኔታ ሲገጥመን ለመረጋጋት ስሜቱን በአፍታ ፍንዳታ ላለማባከን እንሞክር ቀስ በቀስ እያጣጣምነው እድሜው ይራዘም፤ ይህ ከፍተኛ ሐዘን ሲገጥመንም explosion ተፈጥሮ አጓጉል እንዳንሰበር ይረዳናል። የአዕምሮን ሰላም (peace of mind) ለመጠበቅ የሚረዱን ነገሮች- ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መራቅ፤ ፍላጎቶችን መገደብ፤ ራስን ከሌላው ጋር አለማወዳደር፤ ስላሉን በረከቶች ዘወትር ማመስገን፤ የህይወት ትልቁ ስኬት ሰላምና ጤና መሆኑን አለመዘንጋት። ደስታን እንደ ግብ ማሳደድ ሳይሆን ሰላምን እንደ የአሁናዊነት ምንጭ ( source of nowness) እና የሕይወት ሚዛን አድርጎ መቀበል ዘላቂ የሆነ መረጋጋት እና እውነተኛ ደስታን ያስገኛል።
✍ የቃላት ቤት
ውብ አሁን ♥️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot